ዜና

ዜና፡ ሴት መር የሲቪል ማኅበራት በመንግስትና ታጣቂዎች መካከል ድርድር እንዲደረግ እና በድርድር ላይ ሴቶችን ተካታች እንዲደረጉ ጠየቁ

አዲስ አበባ፣ ጥር 30/ 2016 ዓ/ም፡_ በመንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት መካከል የእርቅ ድርድር እንዲቀጥል እንዲሁም ከሌሎች ታጣቂ ኃይላት ጋር ያለዉ ችግር በተመሳሳይ መልኩ በውይይት እንድፈታ ሴት መር አንዲሁም በሴቶች ጉዳይ ላይ የሚሰሩ የሲቪል ማኅበራት ጠየቁ። 

ማህባራቱ ማክሰኞ ባወጡት መግለጫ ሴቶች በግጭቶ በግንባር ቀደምትነት ተጠቂዎች ናቸው ሲል ገልጸው እስካሁን በተደረጉት የፕሪቶሪያ እና የታንዛኒያ ንግግሮች ሴቶች አልተሳተፉም ብለዋል። በመሆኑም መንግሥትም ሆነ ሁሉም ተቃዋሚ ፓርቲዎች የሴቶችን የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሊወስኑ በሚችሉ ውይይቶች ላይ እንዲያተኩሩ አሳስብል። 

በመንግስት እና በኦሮሞ ነጻነት መካከል የተጀመረው ውይይት ያለ ምንም እንቅፋት/እንከን እንዲጠናቀቅ እንደ ሲቪል ማህበራት የድርሻችንን ለመወጣት ዝግጁ ነን ያሉት ማህበራቱ፤ ድርድሩ የሴቶቸችን አካታችነት ባረጋገጠ መልኩ እንዲቀጥልም ጥሪ አቅርበዋል። 

ማህበራቱ “ እኛ በዚህች አገር ሰላም እንዲመጣ እና ሰላም እንዲሰፍን የምንሠራ እንደመሆናችን መጠን በመንግሥት እና በኦነስ መካከል ለረጅም ጊዜ የዘለቀውን አስከፊ ግጭት እና ያስከተለውን ውድመት በመረዳት በውይይት ለመፍታት ወስነው ወደ ውይይት መግባታችሁን እንደግፋለን፣ እናበረታታለን” ሲሉ ገልጸዋል።

“የኢትዮጵያ ህዝብ ለረጅም ጊዜ ተሸክሞት ካለው ሰቆቃ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እንዲያርፍ” ያለስምምነት የተጠናቀቀው የሁለተኛው ዙር በኢትዮጵያ መንግስት እና በኦነስ መካከል የነበረው ድርድር በአጭር ጊዜ እንዲቀጥል፣ አንዲሁም ከሌሎች የታጠቁ አካላትም ጋር ሰላማዊ ስምምነቶች አንዲመሠረቱ ጥሪ አቅርበዋል።

በቀጣይ በሚደረጉ ድርድሮችም ሴቶችን ማሳተፍ እንደሚገባ በአጽንዖት አሳስበዋል።አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button