ዜናፖለቲካማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በኢትዮጵያ 7 ነጥብ 6 ሚሊየን ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጭ መሆናቸውን ዩኒሴፍ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 12/2016 .ም፡ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የህጻናት አድንድ ድርጅት ዩኒሴፍ በቅርቡ ባወጣው ሪፖርት በኢትዮጵያ 7 ነጥብ 6 ሚሊየን ህጻናት ከትምህርት ገበታ ውጨ መሆናቸውን አስታወቀ። ህጻናቱ ከትምህርት ገበታ ውጭ የሆኑት በሰው ሰራሽ እና በተፈጥሮ አደጋ ችግር መሆኑን ጠቁሟል።

በሀገሪቱ ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች 8ሺ 552 የሚሆኑት በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ጉዳት እንደደረሰባቸው የጠቆመው የዩኒሴፍ ሪፖርት ይህም ሃያ በመቶ የሀገሪቱ የትምህርት ቤቶችን መሆኑን አመላክቷል።    

በአማራ እና ኦሮምያ ክልሎች በመካሄድ ላይ ያሉት ግጭቶች በትምህርት ገበታቸው ላይ የማይገኙ የሀገሪቱ ህጻናት ቁጥር እንዲያሻቅብ ከፍተኛ ሚና መጫወቱን በሪፖርቱ ተካቷል።

ህጻናቱ በአፋጣኝ ወደ ትምህርት ገበታ እንዲመለሱ ካልተደረገ እና ጊዜው እየተራዘመ በሄደ ቁጥር ህጻናቱ ወደ መደበኛ ትምህርት የመመለስ እድላቸው እጅግ አነስተኛ ነው ሲል አሳስቧል።

በተጨማሪም ለትምህርት ዘርፍ በጣም ዝቅተኛ የገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት መሆኑን ያልሸሸገው ዩኒሴፍ በአሁኑ ጊዜ 22 በመቶ ብቻ በሚሸፍን ድጋፍ 851,000 ህጻናትን አየተረዱ ነው  ብሏል። ይህ ደግሞ በ2023 በኢትዮጵያ 3.8 ሚሊዮን ህጻናትን ለመርዳት ከታቀደው እጅግ ያነሰ መሆኑን አክሎ ገልጿል።

357,948 ለሚሆኑ ህፃናት የመማሪያ መሳሪያዎቸን በማክፋፈል ችግሩን ለማቃለል ጥረቶች እየትደረጉ መሆኑና አማራ እና ትግራይን ጨምሮ በሁሉም ክልሎች ወድ ትምህርት የመመለስ ዘመቻ ተደርጓል ሲል አስታውቋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button