ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ የፋኖን እንቅስቃሴ በመግታት ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ከመፍረስ ታድጓል ሲል መንግስት ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 22/2016 ዓ.ም፡- የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ እዝ በሰራው ስራ የፋኖን እንቅስቃሴ በመግታት ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ከመፍረስ ታድጓል ሲል መንግስት መግለጹ ተዘገበ።

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትሩ ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ዛሬ ጥቅምት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ለመንግስት መገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ የፋኖ ታጣቂ ቡድን የአማራ ህዝብ ጥያቄን ሽፋን በማድረግ ኢ-ህገመንግስታዊ አካሄድን በመከተል በሃይልና በነፍጥ፣ በረብሻና በግርግር በመታገዝ በመጀመሪያ አማራ ክልልን ከዛም የፌደራል ስርዓቱን በማፍረስ የራሱን እኩይ ኢኮኖሚያ እና ፖለቲካዊ ፍላጎቶች ለማሳካት አልሞ ነበር ማለታቸውን ዘገባዎቹ አመላክተዋል፡፡

ክልሉን ወደ ነበረበት ሰላማዊ ሁኔታ ለመመለስ የተደረጉ ጥረቶችን እና የአመራር መልሶ ማደራጀት ስራዎች መሰራታቸውን እና እነዚህም ስራዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ እዝ እና ሌሎች ተጓዳኝ አደረጃጀቶች ለህዝቡ ግልፅ መደረጉን ሚኒስትሩ ማውሳታቸውን ዘገባዎቹ አካተዋል።

ጥቅምት 21 ቀን 2016 የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጠቅላይ መምሪያ እዝ የእስካሁኑን የትግበራ እንቅስቃሴ መመርመሩን ሚኒስትሩ አስታውቀዋል ያሉት ዘገባዎቹ በዚኅም በግምገማ ማረጋገጥ የተቻለው ህገ መንግስታዊ ስርዓቱን ከመፍረስ መታደጉን ነው ማለታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ከዚህም በላይ በክልሉ የተጠናከረ አመራር እንዲደራጅ እና የህዝቡን መሰረታዊ ጥቄዎች ለመፍታት ቁመና እንዲላበስ መደረጉ በግምገማው ተገጋግጧል ማለታቸውንም አካተዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button