ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በህገወጥ መንገድ ወደ ኬንያ የገቡ 26 ኢትዮጵያውያን ሴቶች በፖሊስ መያዛቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 30/2015 .ም፡ የኬንያ ሙራንጋ አውራጃ ፖሊስ በህገወጥ መንገድ ወደ ግዛቱ የገቡ 26 ኢትዮጵያውያን ሴቶችን በቁጥጥር ስር መዋሉን የኬንያ መገናኛ ብዙሃን በዘገባቸው አስታውቀዋል። እድሜያቸው ከ22 እስከ 32 የሚደርሱ ኢትዮጵያውያኑ ግንባታው ባላለቀ አንድ የመኖሪያ ህንጻ ተደብቀው መገኘታቸውን ዘገባዎቹ አመላክተዋል።

የሙራንጋ አውራጃ የፖሊስ ኮማንደር ዴቪድ ማቲው ካይንጋ የተመራው ቡድን ከአከባቢው በደረሰው ጥቆማ መሰረት በህንጻው ላይ ባካሄደው አሰሳ ኢትዮጵያውያኑን ከነፓስፖርታቸው እና ከ16 የሞባይል ስለኮቻቸው ጋር መያዙን ያስታወቁት ዘገባዎቹ ሴቶቹ ወደ ደቡብ አፍሪካ በማቅናት ላይ እንደነበሩ መገለጹን አስታውቀዋል።

በህገወጥ መንገድ ሴቶቹን ወደ ኬንያ ያስገቧቸው እና ወደ ደቡብ አፍሪካ የሚወስዷቸው ህገወጥ አዘዋዋሪዎች ከሴቶቹ ጋር አለመገኘታቸውን ዘገባዎቹ አመላክተዋል።

ሴቶቹ ተጠልለውበት የነበረው ህንጻ ባለቤት እና ጠባቂው በፖሊስ ተይዘው ምርመራ እየተደረገባቸው እንደሚገኝ መገናኛ ብዙሃኑ አስታውቀዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button