ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ ኖርዌ ኢትዮጵያ በቀጣይ 10 አመታት ለምትተገብረው የደን ልማት የሚውል 162 ሚሊየን ዶላር እንደምትሰጥ አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ጳጉሜን 1/2015 .ም፡ የኖርዌ መንግስት ኢትዮጵያ እያካሄደችው ያለውን የደን ልማት ለማገዝ የሚውል 162 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ለመስጠት መወሰኑን አስታወቀ።

በኬንያ ናይሮቢ በመካሄድ ላይ ባለው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የተሳተፉት የኖርዌ የከባቢ አየር ንብረት ሚኒስትር ኢስፐን ባርዝ ኤይዲ እንዳስታወቁት ኢትዮጵያ የምታካሂደውን የደን ልማት ለማገዝ ሀገራቸው የ25 ሚሊየን ዶላር እንደምትሰጥ ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ እያካሄደች ያለውን የደን ልማት እውቅና እንሰጣለን ያሉት ሚኒስትሩ ሰፊ የሀገሪቱ የደን ክፍል ከአልባሌ ውድመት የተጠበቀ መሆኑን ጠቁመዋል። ይህም የአከባቢው ነዋሪዎች፣ ሀገሪቱን እና በስፋትም ቀጠናው ላይ የሚጠቅም ተግባር ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ሀገራቸው ኢትዮጵያ በቀጣይ አስር አመት በደን ልማት ላይ ለምታደርገው ልማት የሚውል 162 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር እንደምትሰጠው ያመላከቱት ሚኒስትሩ ይህም ኢትዮጵያ በቀጣይ የተመናመነውን አንድ ሚሊየን ሄክታር የደን ሀብት እንዲያገግም ለማድረግ ያስችላታል ብለዋል። 75ሺ ሄክታር የሚደርስ ከፍተኛ ጠቀሜታ ያላቸው የደን ሀብቶችን ለማስጠበቅ ያስችላታል ሲሉም ገልጸዋል፤ ይህም 300ሺ የሚደርሱ ቤተሰቦችን ለመፍጠር እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።   

ኦክስፋም ከአየር ንብረት ለውጥ ካስከተለው ቀውስ ጋር በተያያዘ አራት የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ማለትም ኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ሶማሊያ እና ደቡብ ሱዳን ከ2013 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አመታት ብቻ 30 ቢሊየን ዶላር መክሰራቸውን አስታውቋል። በአለም አቀፍደረጃ ለተከሰተው የአየር ንብረት ቀውስ ምንም አይነት አስተዋጽኦ የሌላቸው ሀገራት ማለትም እንደ ምስራቅ አፍሪካ ያሉ ሀገራት በዚህ ደረጃ ኪሳራ ሲያስተናግዱ ዋነኛዎቹ በካይ ሀገራት ግን ለእነዚህ አገራት የለገሱት ገንዘብ እጅግ አነስተኛ መሆኑንም አስታውቋል፤ 2 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር ብቻ መለገሳቸውን ጠቁሟል።

አራቱ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ብቻ በአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ምክንያት በሞቱ የቀንድ ከብቶቻቸው 7 ነጥብ 4 ቢሊየን ዶላር መክሰራቸውን ኦክስፋም በሪፖርቱ አመላክቷል።

የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በአየር ንብረት ለውጥ ተጽእኖ ሳቢያ ከሚደርስባቸው ጉዳት እንዲያገግሙ ለማስቻል 8 ነጥብ 7 ቢሊየን ዶላር እንደሚያስፈልጋቸው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ያስቀመጠው ግምት ያሳያል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በኬንያ ናይሮቢ በመካሄድ ላይ ባለው የአፍሪካ የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ላይ የተባበሩት አረብ ኤሚሬት ለአፍሪካ የታዳሽ ሀይል ልማት የሚውል 4 ነጥብ 5 ቢሊየን ዶላር ለመለገስ ቃል መግባቷ ተገልጿል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button