ዕለታዊፍሬዜናፖለቲካ

ዜና፡ አካታችና ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ኃይሎች ውይይት በአስቸኳይ እንዲደረግ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 17/2015 ዓ.ም፡- መንግስት እየወሰደ ያለው የኃይል እርምጃም ሆነ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ “ዘላቂ መፍትሄ የማያመጣ” በመሆኑ አካታችና ሁሉን አቀፍ (የታጠቁትን ጨምሮ) የፖለቲካ ኃይሎች ውይይት በአስቸኳይ እንዲደረግ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ አሳሰበ፡፡

ተቃዋሚ ፓርቲዎች ኮከስ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ነሃሴ 12 ግምገማ አድርጎ ዛሬ ይፋ ባደረገው መግለጫ እየተወሰዱ ያሉ የኃይል እርምጃዎችንና የመሳሪያ ግጭቶችን አጥብቆ እንደሚያወግዝ አስታውቋል፡፡ በተጨማሪም ወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይን በተመለከተ ሀገራችንና ህዝባችን በእጅጉ አሳሳቢና አፋጣኝ የዘላቂ መፍትሄ እርምጃ የሚጠይቁበት ደረጃ ላይ ናቸው ሲል በመግለጫው ገልጧል፡፡

የተቃዋሚ ፓርቲዎቹ መግለጫ ከዚህ በፊት በነበሩ ግጭቶችና ችግሮች እንዲሁም ከነዚህ ግጭቶች ጋር በተያያዘ መንግስት በተለያየ ጊዜ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በማውጣት በኃይል እርምጃ መፍትሄ ለማምጣት ቢሞክርም ፖለቲካዊ ያለመረጋጋቱንና ውጥረቱን፣ ኢኮኖሚያዊ ጥፋትና ውድመቱን እልቂቱንና ማኅበራዊ ቀውሱን ከማስፋትና ከማባባስ አልፎ ዘላቂ መፍትሄ አላመጣም ብሏል፡፡

ስለሆነም ኮከሱ መፍትሄ ይሆናል ያለውን፣ በመንግስት ኦነግ ሸኔ የሚባለው ራሱን የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት (ኦነስ) ብሎ በሚጠራ ኃይልና በመንግሥት ኃይል መካከል የተጀመረው ውይይት ድርድር ዳግም በግልጽና አካታች ሁኔታ እንዲቀጥል ጥይቋል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የአማራ ክልል የመንግስትና የአማራ ህዝባዊ ሃይል ግንባር ግጭት እንዲያቆሙና ውይይት (ድርድር) እንዲጀምሩ እንዲሁም የትግራይ ክልል ጉዳይ በስምምነቱ መሰረት እንዲፈጸምና መፍትሄ እንዲያገኝ አበክሮ ጠይቋል፡፡

በተጨማሪ “ገዢው ፓርቲ ለዚህ ቀና ሀገር አድን ጥሪ አዎንታዊ ምላሽ በመስጠት የሀገራችን የፖለቲካ አስተሳሰብና ልምድ እንዲሻሻልና እንዲያድግ፣ ካለፈው የመማር ልምድ የመማር ልምድ መሰረት እንዲጣል በማድረግ የፖለቲካ ታሪካችን ላይ በጎ አሻራውን እንዲያሳርፍ” ጥሪ ማስተላለፉን በመግለጫው ተመላክቷል፡፡

በመጨረሻም ኮከስ የታጠቁ ኃይሎች በሙሉ ለሠላማዊ ዘላቂ መፍትሄ የምናደርገውን ጥሪ በአዎንታዊነት እንዲቀበሉ፣ ትግላቸውም ከሥርዓት ለውጥ አልፎ በህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ላይ ጥቁር አሻራ እንዳያሳርፍ አስፈላጊውን ጥንቃቄና የአብሮነት ማረጋገጫ እርምጃ እንዲተገብሩ ጥሪ አስተላልፏል፡፡

የሚዲያ ተቋማት፣አክቲቪስቶችና የሀገሪቱ ፖለቲካ ባለድርሻ አካላት በሙሉ በሀገራችን እየታየ ያለው አሳሳቢ ሁኔታ በህዝብ መካከል የተፈጠረ ችግር በሚመስል መልክ በማቅረብ ቀጣይ አንድነታችንና አብሮነታችን ላይ ጠባሳ ከማሳደር አልፈው የሥርዓቱን ዕድሜ እንዳያራዝሙና የተለመደውን የፖለቲካ አስተሣሰብና ልምድ ከማስቀጠል እንዲቆጠቡ ያሳሰበው ተቃዋሚ ፓርቲዎቹ የኃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎች ህዝባችን በሚጠብቃቸው ቦታ ተገኝተው ማኅበራዊ ኃላፊነታቸውን በአግባቡ እንዲወጡ ጥሪውን አስተላልፏል፡፡አስ

 

 

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button