ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ ሶስት የሞስኮ ትምህርት ቤቶች አማርኛ እና ስዋሂሊ ቋንቋዎች ማስተማር እንደሚጀምሩ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 26/2015 ዓ.ም፡- በሩሲያ የትምህርት ዘመን በቀጣይ ሳምንት ይጀምራል። የሞስኮ የትምህርት እና ሳይንስ ክፍል እንዳስታወቀው ከሆነ በቀጣይ ሳምንት በሚጀምረው አዲሱ የትምህርት ዘመን ሶስት የሞስኮ ከተማ ትምህርት ቤቶች አማርኛ እና ስዋሂሊ ቋንቋን እንዲያስተምሩ ይደረጋል።

ሁለቱን የአፍሪካ ቋንቋ በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ማስጀመር የተፈለገበት ዋና አላማ በቀጣይ የሀገሪቱ ተማሪዎች ስለ አፍሪካ ለማጥናት ፍላጎት እንዲያድርባቸው ለማስቻል መሆኑን የሞስኮ የትምህርት እና ሳይንስ ክፍል ማመላከቱን ስፑትኒክ የተሰኘው የሩሲያ ሚዲያ በድረገጹ አስነብቧል።

ቋንቋውን የሚያስተምሩ መምህራኑ ዝግጁ መሆናቸውን የከተማዋ የትምህርት ክፍል አስታውቋል ያለው ዘገባው በከተማዋ የሚገኘው የትምህርት ቤቱ መለያ 1522 አማርኛ ትምህርትን ለአንድ ቡድን ተማሪዎች እንደሚሰጥ አስታውቋል። የትምህርት ቤቱ መለያ 1517 ደግሞ የስዋሂሊ ቋንቋን እንደ ሁለተኛ ቋንቋ እንደሚያስተምር ተገልጿል።

እንደ የሞስኮ የትምህርት እና ሳይንስ ክፍል መግለጫ ከሆነ የቋንቋ ማስተማሩ ዋነኛ አላማው ተማሪዎቹ የአፍሪካን ቋንቋ እንዲማሩ ሳይሆን ለወደፊት በአፍሪካ ጥናት ላይ ፍላጎት እንዲያድርባቸው ለማስቻል መሆኑን አመላክቷል።

የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት በሞስኮ ትምህርት ቤቶች ከመስከረም ጀምሮ እንደሚሰጥ የስፑትኒክ ዓለም አቀፍ የዜና አገልግሎት ድርጅት እና ሬዲዮ፤ በሩሲያ – አፍሪካ የኢኮኖሚ ትብብር ተስፋዎች ዙሪያ ከሶስት ወራት በፊት ውይይት ባካሄደበት ወቅት መገለጹ ይታወሳል።

ውይይቱ በአሌክሳንደር ጎርቻኮቭ ፐብሊክ ዲፕሎማሲ ፈንድ እና በሰብአዊ እርዳታ ማእከል ድጋፍ የተዘጋጀ ሲሆን÷ በሩሲያ እና በመካከለኛው ምስራቅና በአፍሪካ ሀገራት መካከል አዲስ የትብብር አድማስ” ለመፍጠር ያለመ የባለሙያዎች እና ትምህርታዊ ዝግጅት አካል መሆኑ ተጠቁሟል። በውይይቱ ላይ ከሩሲያ እና አፍሪካ የተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች የተውጣጡ የታሪክ ተመራማሪ ምሁራንና የሥራ ኃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

የእስያ እና አፍሪካ ጥናት ኢንስቲትዩት ዳይሬክተር አሌክሲ ማስሎቭ ከፈረንጆቹ መስከረም 2023 ጀምሮ ቢያንስ አራት የሞስኮ ትምህርት ቤቶች ለህጻናት የአማርኛ እና የስዋሂሊ ቋንቋ ማስተማር እንደሚጀምሩ ይፋ አድርገዋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button