ዜናማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ አዲስ አበባ ከፍተኛ የተፈጥሯዊ አደጋ ስጋት እንዳንዣበበባት ተገለጸ፤ ከፍተኛ ሙቀት፣ ድርቅ እና ጎርፍ ዋነኛ ስጋቶቿ ናቸው ተብለዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 3/2016 .ም፡ አዲስ አበባ በቀጣይ 67 አመታት ከፍተኛ የተፈጥሮ አደጋ ስጋት እንደተደቀነባት አንድ ጥናት አመላከተ። የከተማዋ ዋነኛ ስጋቶች ተብለው ከተጠቀሱት መካከል ከፍተኛ ሙቀት፣ ድርቅ እና ጎርፍ ይገኙበታል።  እነዚህ ስጋቶች የከተማዋን ህዝብ የጤና ሁኔታን እና መሰረተ ልማቶቿ ላይ አደጋ እንደሚፈጥሩ ጥናቱ ጠቁሟል።

ቱፍት ዩኒቨርስቲ እና ውድ ዌል ክላይሜት ሪሰርች ሴንተር በጋራ በከተማዋ የአየር ንብረት ሁኔታ ላይ ያጠኑት ጥናት እንደሚያመላክተው ከተማዋ የሚያጋጥማት የተፈጥሮ አደጋ በዋነኛነት ተጽእኖውን የሚያሳድረው በኢመደበኛ አሰፋፈር በከተማዋ የሚኖሩት ላይ መሆኑን ያሳያል።

የከተማዋ የህዝብ ብዛት 5 ነጥብ 4 መሆኑን እና በ2035 9 ሚሊየን እንደሚደርስ መተንበዩን የጠቆመው የጥናቱ ዘገባ አብዘሃኛው በከተማዋ የሚኖረው አሰፋፈር ኢመደበኛ መልክ እንደሚኖረው እና ስደተኞች እንደሚበዙበት አስታውቋል።

ኢመደበኛ አሰፋፈሮች በባህሪያቸው እጅግ አነስተኛ ወይን የለም ሊባል የሚያስችል መሰረተ ልማት የተላበሱ መሆናቸውን የጠቀመው ጥናቱ የአየር ንብረት መዛባት እና ደካማ የከተማ አየር ንብረት ፖሊሲ ተዳምረው ስጋቱን ከፍተኛ እንደሚያደርጉት ገልጿል።

የከተማዋን ለተፈጥሮ አደጋ ስጋት ተጋላጭነት ለመመርመር ጥናቱን ያካሄዱት ቱፍት ዩኒቨርስቲ እና ውድ ዌል ክላይሜት ሪሰርች ሴንተር ተመራማሪዎች በተለያዩ ገዜያት በከተማዋ የተመዘገቡ የሙቀት መጠኖችን እና የጎርፍ ተጋላጭነቷን መተንተናቸውን አስታውቀዋል። ጥናቱን ያደረጉት ተቋማት ባስቀመጡት ትንበያ መሰረት የከተማዋ የሙቀት መጠን ከ2040 እስከ 2060 በአንድ ነጥብ ሰባት ዲግሪ ሴንቲግሬድ ጭማሪ ይኖረዋል።  ይህም በከተማዋ የጤና፣ የመሰረተ ልማት፣ አናኗር ዘይቤ፣ እና የምግብ አቅርቦት እና ስነ ምህዳር ላይ ትልቅ ስጋት ይፈጥራል ተብሏል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button