ዜናፖለቲካ

ዜና፡ መንግስት በቀጣይ ሶስት አመታት የህዝብና ቤት፣ የኢኮኖሚ እንዲሁም የግብርና ቆጠራ ለማድረግ ማቀዱን ይፋ አደረገ

አዲስ አበባ፣ ጥር 23/2016 ዓ.ም፡- መንግስት ጥራት ያለዉ መረጃ ለማመንጨት እንዲሁም በመረጃ ላይ የተመሰረተ ዉሳኔን ለማስተላለፍ የሚያግዘኝ በሶስት ዓመታ የሚተገበር የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ ልማት ፕሮግራም ይፋ አድርጊያለሁ አለ።

በፕሮግራሙ የሶስት ዓመታት ቆይታም የኢኮኖሚ ቆጠራ፣ የግብርና እንዲሁም የህዝብና ቤት ቆጠራ ለማድረግ አቅጃለሁ ያለው መንግስት ፕሮግራሙ በፕላንና ልማት ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት የተዘጋጀ መሆኑን ጠቁሟል።

የግብርና ቆጠራ የተደረገው ከ25 ዓመታት በፊት መሆኑን በፕሮግራሙ ይፋ ማድረጊያ ላይ ንግግር ያደረጉት የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶ/ር ፍጹም አውስተዋል ያለው ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ በፕሮግራሙ የሚደረገዉ የግብርና ቆጠራ በግብርና ስርአቱ ዉስጥ የገቡ የበጋ የስንዴ ልማትን ጨምሮ የተደራጀ የግብርና ዘርፍ መረጃ እንዲኖር ያደርጋል ማለታቸውነ አስታውቋል።

የህዝብና ቤት ቆጠራ ለማድረግ መንግስት ከፍተኛ ፍላጎት አለዉ ያሉት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ በአለማቀፍ መስፈርት መሰረት ቆጠራዉን ለማድረግ የሚያስቺሉ ሁኔታዎች ባለመኖራቸዉ እስካሁን ማድረግ አለመቻሉን አንስተዋል።

አሁን የሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት በፕሪቶሪያዉ ስምምነት ወደ ሰላም መምጣትና “የአማራ ክልልን ጨምሮ ሌሎች አካባቢዎም ያለዉ ሰላም እየተሻሻለ በመምጣቱ” እቅዱ በፕሮግራሙ ዉስጥ መቀመጡን ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

ቆጠራዉን ለማከናወን ከፍተኛ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ስለሚጠይቅም የቅድመዝግጅት ስራዎች መጀመራቸዉንም ተናግረዋል። ፕሮግራሙ የሁለተኛዉ የሃገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርምና የመካከለኛ ዘመን የኢንቨስትመንት እቅድ አካል መሆኑንም ክብርት ሚኒስትር ተናግረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ የፕሮግራሙን አጠቃላይ ይዘትና አተገባበር በተመለከተ ለመድረኩ ገለጻ ማድረጋቸውን የጠቆመው የሚኒስቴሩ መረጃ በመድረኩ የተገኙ ሚኒስትሮች ፣ የተቋማት መሪዎች ፣ የክልሎች ተወካዮች እና የተለያዩ አለማቀፍ ተቋማት የስራ ሃላፊዎች በቀረቡ የፕሮግራሙ ገለጻ ላይ አስተያየቶችን ሰጥተዋል ብሏል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button