ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በትግራይ ለውጥ ለማምጣት የሚያደርጉትን የጥምረት ትግል እንደሚቀጥሉበት በክልሉ የሚንቀሳቀሱ ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 5/2016 .ም፡ ትግላችን የአንድ ቀን ሳይሆን ቀጣይነት ያለው እና የማይቀለበስ ነው ሲሉ በትግራይ የሚንቀሳቀሱ ሶስት የፖለቲካ ፓርቲዎች በጋራ ባወጡት መግለጫ አስታወቁ። በትግርኛ “ኪዳን ንሱር በቆስ ለውጢ” በሚል መሪ ቃል የስርነቀል ለውጥ ጥምረት በሚል በሶስቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች የትግራይ ነጻነት ፓርቲ፣ ሳልሳይ ወያነ ትግራይ እና ብሔራዊ ባይቶና ትግራይ ፓርቲዎች በጋራ ያስጀመሩት ትግል ክልሉን እያስተዳደረ በሚገኘው ሀይል ለጊዜው የተገታ ቢመስልም አጠናክረን እንቀጥላለን ብለዋል።

ፓርቲዎቹ በክልሉ ዋና ከተማ መቀለ ከጳጉሜን 2 እስከ 4 ቀን 2015 ዓ.ም ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ ሲያደርጉ እንደነበር በመግለጫቸው አስታውሰው በመጀመሪያው ቀን ክልሉን የሚያስተዳድረው ሀይል ሰልፉን ለማካሄድ በመጡ የከተማዋ ነዋሪዎች ላይ ከድብደባ እስከ ግድያ ሙከራ በመፈጸም እንዲስተጓጎል ማድረጉን አስታውቀዋል።

ከጅምሩ ጀምሮ ለፖለቲካ ለውጥ የጠራነውን ሰልፍ አገዛዙ የአመጽ ሰልፍ ነው በሚል የስም ማጥፋት ዘመቻ አካሂዶብናል ሲሉ የተቹት ፓርቲዎቹ ይህንን የአገዛዙን ፕሮፓጋንዳ አንቀበልም ብለው በወጡ ወጣቶች ላይ ከፍተኛ ድብደባ መፈጸሙን በመጥቀስ ኮንነዋል።

ለስርነቀል ለውጥ በጥምረት የጀመርነው ትግል የአንድ ቀን አይደለም ሲሉ በመግለጫቸው ያስታወቁት ፓርቲዎቹ በቀጣይነት እየሰፋ እና እየተጠናከረ ይሄዳል ብለዋል። ወደ አደባባይ የወጣውን የትግራይ የፖለቲካ ፓርቲዎችን ትግል ወደ ኋላ የሚመልሰው አይኖርም ብለዋል። ፓርቲዎቹ በመጨረሻም በጥምረት እያካሄዱት ስላለው ትግል ዝርዝር መግለጫ እንደሚሰጡ ጠቁመዋል።

ሶስት የትግራይ ፓርቲዎች ሳልሳይ ወያነ ትግራይ፣ ብሄራዊ ባይቶ ዓባይ (ባይቶና) እና ውድብ ናፅነት ትግራይ በተከታታይ ከጳጉሜ 2 አስከ 4 /2015 ዓ.ም በመቐለ ከተማ የአደባባይ የተቋወሞ ስልፍ ለማካሄድ ያስተላለፉን ጥሪ የከተማ አስተዳደር መከልከሉ ተገቢ ባለመሆኑ ሰላማዊና ለውጥ ፈላጊውን ህዝባችን ይዘን በያዝነው የግዜ ሰሌዳ ሰልፉን እናካሄዳለን ሲሉ መግለጻቸውን መዘገባችን ይታወሳል፡፡

በወቅቱ ሊደረግ በነበረው የተቃውሞ ሰልፍ ጋር በተያያዘ የክልሉ ፖሊስ የብሄራዊ ባይቶ ዓባይ (ባይቶና) መሪ እና የሰልፉ አስተባባሪ የሆኑት ኪዳነ አመነ እና ተስፋሚካዔል ንጉስን ጨምሮ በርካታ የፓርቲዎቹን አመራሮች እና አስተባባሪዎች አስሮ መልቀቁ ተዘግቧል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button