ዜናፖለቲካ

ዜና፡ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት በኢትዮጵያና በሶማሌ ላንድ መካከል የተፈረመውን ስምምነት “ያለልዩነት” እንደሚደግፍ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 2/ 2016 ዓ/ም፡_ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት በኢትዮጵያና በሶማሌ ላንድ መካከል የተፈረመውን መግባቢያ ሰነድ ስምምነት “ያለልዩነት” እንደሚደግፍ አስታወቀ። 

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ እና የሶማሊ ላንዱ ፕሬዝዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ፤ ኢትዮጵያ የባህር በር እና የባህር ኃይል ቤዝ ለመገንባት የሚያስችላትን 20 ኪሎ ሜትር የባህር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ትላንት ባወጣው መግለጫ በሁለቱ ሀገራት መካከል የተፈረመውን  “የስምምነቱን ማዕቀፍ፣ ዝርዝር ይዘቱን እና ከስምምነቱ ጋር ተያይዞ ባሉት እድሎችና ስጋቶች ላይ በዝርዝር ከተወያየን በኋላ ስምምነቱን ያለልዩነት የምንደግፍ መሆናችንን ጥር 01፣ ቀን 2016 ዓ.ም በተደረገው ጠቅላላ ጉባዔ አረጋግጠናል” ብሏል። 

ም/ቤቱ በመግለጫው “ከተግባራዊነቱ አንፃር የሚኖሩትን ውስጣዊ እና ውጫዊ ስጋቶችን እና እድሎችን በዝርዝር መክረን ለስምምነቱ ውጤታማነት በጋራ በመቆም ሚናችንን ለመወጣት ያለንን ቁርጠኝነት ዳግም እናረጋግጣለን” ሲል አክሏል።  መንግስት ፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና መላው ህብረተሰባችን የበኩላቸውን አውንታዊ ሚና እንዲወጡ ሲልም ጥሪ አቀርቧል። 

ከዚህ በተጨማሪም ሀገራዊ ምክክር ውጤታማነት እንቅፋት የሆኑ ጉዳዮችን በመፍታት እና አስፈላጊውን ድጋፍ ሁሉ በማጠናከር ለመቀጠል በተደረገው ጠቅላላ ጉባዔ ወሳኔ ላይ መደረሱን አስታወቋል። እንደ መግላጫው ገለጻ፣ አካታች ሀገራዊ ምክክሩ ስራው የደረሰበትን ደረጃ ፣ ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን እና በመፍትሄ አቅጣጫወች ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ሚናን አስመልክቶ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሪፓርትና ማብራሪያ  ቀርቦ  ውይይት ተደርጎ ውሳኔው ላይ ተደርሷል። 

በመጨረሻም የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ም/ቤት ለምክክር ኮሚሽኑ ተልዕኮ ስኬት እንቅፋት እየሆነ ያለውን የሰላምና የጸጥታ ችግር በመቅረፍ መንግስት፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና  መላው ህዝቡ እንዲረባርብ እና ሂደቱ ሁሉም የሀገሪቱ የፖለቲካ ፓርቲዎች እንዲሳተፉ ጥሪ አቀርቧል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button