ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ ኢትዮጵያ ከአፍሪካ ሶስተኛዋ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ ተጠልሎባት የምትገኝ ሀገር መሆኗ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 1/2016 ዓ.ም፡- ለበርካታ አመታት በአፍሪካ በአንደኛ ደረጃ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ አስጠልላ የቆየችው ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ሶስተኛዋ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ ተጠልሎባት የሚገኝ ሀገር ናት ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት ዩኤንኤችሲአር አስታወቀ።

ሱዳንን እና ኡጋንዳን በመከተል በሶስተኝነት ስደተኞችን ያስጠለለችው ኢትዮጵያ 954ሺ ከተለያዩ ሀገራት ድንበሯን አቋርጠው የገቡ ስደተኞች እንደሚገኙባት ተቋሙ ይፋ ባደረገው መረጃ ጠቁሟል።

የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት ዩኤንኤችሲአር ይፋ ያደረገው መረጃ እንደሚያመላክተው በኢትዮጵያ ተጠልለው ከሚገኙ ስደተኞች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የሚይዙት ሱዳናውያን ናቸው። ከሶማሊያ እና ከኤርትራ ተሰደው በኢትዮጵያ የተጠለሉ ስተኞች በሁለተኝነትእና በሶስተኝነት ተቀምጠዋል።

ኢትዮጵያ በሁሉም ድንበሮቿ የጎረቤት ሀገራት ስደተኞች እንዲገቡ በሮቿን ክፍት ማድረጓን የጠቆመው የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት ዩኤንኤችሲአር ከፌደራል መንግስት እና ከክልል ባለስልጣናት ጋር በመተባበር ስደተኞቹ አስፈላጊው የሆኑ ነገሮች እንዲሟሉላቸው እየጣረ እንደሚገኝ አመላክቷል።

በኢትዮጵያ ተጠልለው ከሚገኙት 954ሺ ስደተኞች መካከል ከ417ሺ የሚሆኑት ከደቡብ ሱዳን፣ ከ308ሺ የሚሆኑት ከሶማሊያ፣ 168ሺ የሚሆኑት ከኤርትራ፣ 50ሺ የሚሆኑት ከሱዳን፣ 4ሺ የሚሆኑት ከኬንያ፣ 2ሺ 500 የሚሆኑት ከየመን፣ አንድ ሺ የሚሆኑት ከዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ፣ 671 የሚሆኑት ከሶርያ መሆናቸውን የመንግስታቱ ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ መስሪያ ቤት መረጃ ያሳያል።

805 ሺ የሚሆኑት ስደተኞች በሀገሪቱ በሚገኙ የስደተኛ ካምፖች እንደተጠለሉ የጠቆመው የተቋሙ መረጃ ከ76ሺ በላይ የሚሆኑት ደግሞ በተለያዩ የሀገሪቱ ከተሞች ኑሯቸውን ማድረጋቸውን አመላክቷል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button