ዜናማህበራዊ ጉዳይቢዝነስ

ዜና፡ የመኪና ጭስ ስታንዳርድ እየተዘጋጀ በመሆኑ አሮጌ መኪና ያላቸው አሽከርካሪዎች አስቀድመው መፍትሄ እንዲያዘጋጁ ባለሥልጣኑ አሳሰበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 10/2016 ዓ.ም፡- በአዲስ አበባ ከፍተኛ ጭስ የሚለቅ መኪና ያላቸው አሽከርካሪዎች አስቀድመው መፍትሄ እንዲያዘጋጁ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ጠየቀ። የመኪና ጭስ ስታንዳርድ እየተዘጋጀ መሆኑንም ገልጿል።

የመኪና ጭስ ስታንዳር እየተዘጋጀ መሆኑ እና እያንዳንዱ መኪና የሚያስወጣው ጪስ እንደሚለካ የአዲስ አበባ አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ አቶ ድዳ ድሪባ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረዋል።

ስታንዳርዱ በቅርቡ ተግባራዊ ስለሚደረግ አሮጌና ከፍተኛ ጭስ የሚለቅ መኪና ያላቸው አሽከርካሪዎች ጭስ የሚቀንስ ቴክኖሎጂን መጠቀም ወይም መኪናውን መቀየር ይኖርባቸዋል ተብሏል።

መኪናው ከተቀመጠው መለኪያ በላይ ጪስ የሚያመነጭ ከሆነ አገልግሎት እንዳይሰጥ ይደረጋል ብለዋል። አብዛኛውን ጊዜ ከፍተኛ ጭስ የሚለቁ ተሽከርካሪዎች ከተመረቱ 23 ዓመትና ከዚያ በላይ ያገለገሉ ናቸው ያሉት ኃላፊው፤ ስለዚህ አሮጌ መኪና ያላቸው አሽከርካሪዎች ከአሁኑ መፍትሄ ሊያዘጋጁ ይገባል ብለዋል።

በመዲናዋ አሮጌና ከፍተኛ ጭስ የሚለቁ በርካታ መኪኖች መኖራቸውን በመጥቀስ፤ መኪናዎቹን በአንድ ጊዜ ሥራ እንዲያቆሙ ማድረግ እንደማይቻል አመላክተዋል፡፡

ሆኖም ቦሎ የሚሰጡ፣ መኪናዎችን የሚቆጣጠሩና መኪና የሚገዙ አካላት ባለሥልጣኑ የሚያወጣውን የጭስ ስታንዳርድ መሠረት እንዲያደርጉ አቶ ድዳ አሳስበዋል።

እየተዘጋጀ ያለው የመኪና ጭስ ስታንዳርድ ለአየር መበከል አስተዋጽኦ የሚያደርጉ ጋዞችና ብናኞች ጋር ተያይዘው የሚመጡ የጤና ችግሮችን ለመቀነስ ያስችላል ብለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በመዲናዋ የአየር ጥራት ለመቆጣጠር የሚያስችሉ 10 ዘመናዊ መሣሪያዎች የተገጠሙ ሲሆን በቅርቡ ደግሞ ከመኪና የሚወጣውን ጭስ መቆጣጠር የሚያስችል መሳሪያ ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡ አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button