ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በአልሸባብ እና በኢትዮጵያ ሰራዊት መካከል ውጊያ መደረጉ ተገለጸ፣ አልሸባብ በርካታ የኢትዮጵያ ወታደሮችን ገደልኩ፣ ማረኩ ብሏል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7/2016 .ም፡ በሶማሊያ የሰፈረው የኢትዮጵያ ሰራዊት አባላት በምዕራብ ሶማሊያ ራብ ዱሁር ከተማ ከአለሸባብ ጋር ከፍተኛ ውጊያ ማካሄዳቸውን ነዋሪዎችን ጠቅሶ ሮይተርስ የዜና ወኪል አስታውቋል።

በኢትዮጵያ አቅራቢያ በምትገኘው እና በሶማሊያ በኮለ ግዛት ራብ ዱሁር ከተማ አለሸባብ በአከባቢው በሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ሰራዊት መኪና ላይ በፈጸመው የደፈጣ ጥቃት ግጭቱ መጀመሩን የዜና አውታሩ ገልጿል።

አልሸባብ በአከባቢው በሚንቀሳቀሱ የኢትዮጵያ ወታደሮች መኪና ላይ በፈጸመው ጥቃት ሶስት ከፍተኛ ፍንዳታ መስማታቸውን እና ከዚያም በመቀጠል ከፍተኛ በመሳሪያ የተደገፈ ውጊያ መካሄዱን ነዋሪዎቹ መግለጻቸውነ አመላክቷል።

በተያያዘ ዜና የሩሲያው ስፑትኒክ ሚዲያ በድረገጹ አልሸባብ በፈጸመው ጥቃት 167 የኢትዮጵያ ወታደሮችን ገደልኩ ማለቱን የሶማሊያ መገናኛ ብዙሃንን ዘገባ ዋቢ በማድረግ አስታውቋል። ከጥቃቱ የተረፉትንም ማርኪያለሁ ማለቱን የጠቆመው ዘገባው በተጨማሪም በርካታ መሳሪያ ማረኪያለሁ ማለቱን አመላክቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button