ህግ እና ፍትህዜና

ዜና፡ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ ዞን በተፈጸመ ጥቃት የቀበሌ አስተዳዳሪና የፓርቲ ኃላፊ መገደላቸው ተገለጸ 

አዲስ አበባ፣ መስከረም 7/2017 ዓ/ም፦ በኦሮሚያ ክልል በምስራቅ ወለጋ ዞን ኪራሙ ወረዳ መስከረም 4/2017 ዓ.ም.በተፈጸመ ጥቃት የአካባቢው አስተዳዳሪ እና የፓርቲ ሃላፊ መገደላቸው ተገልጿል።

ጥቃት አድራሾቹ “የፋኖ ሚሊሻዎች ናቸው” ሲሉ የገለጹት የስፍራው ነዋሪዎች አንድ ሌላ የአካባቢው አስተዳዳሪ መቁሰሉን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

በአካባቢው ነዋሪ የሆኑት አቶ ግርማ ተፈራ እንደገለፁት ጥቃቱ የተፈፀመው በኪራሙ ወረዳ፤ መርጋ ጅሬኛ ቀበሌ ልዩ ስሙ ኩቲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው።

የተጎጂ ዘመድ የሆኑት አቶ ግርማ ተፈራ እንዳሉት ሟቾቹ የሲሬ ዶሮ አስተዳደር ሃላፊ የሆኑት አቶ አላምሮ ረታ እና በሲሬ ዶሮ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ መሪ የነበሩት አቶ አክሊ ፍቃዱ ናቸው። 

አቶ ግርማ አክለውም በጥቃቱ በሲሬ ዶሮ ከተማ የብልጽግና ፓርቲ ሃላፊ የነበሩት አቶ አኪሌ ፍቃዱ ከባድ ጉዳት እንደደረሰባቸው እና ህይወታቸው እስካለፈበት መስከረም 5/ 2017 ዓ.ም. ድረስ በህክምና ላይ እንደነበሩ ገልጸዋል። 

ጥቃቱ ከተፈጸመ በኋላ አላምሮ ረታ ወዲያው ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን፤ የመርጋ ጅሬኛ ቀበሌ አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ መርጋ አለሙ በኪራሙ ሆስፒታል በህክምና ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል።

ለደህንነት ሲባል ስማቸው እንዳይጠቀስ የጠየቁ ሌላኛው የመርጋ ጅሬኛ ቀበሌ ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደገለፁት፤ ጥቃቱ የተፈጸመው ተጎጂዎቹ ከኪራሙ ወረዳ በሞተር ሳይክል ተጭነው ለስራ ግዳጅ ወደ ሲሬ ዶሮ ከተማ ሲጓዙ ነበር።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በቅርቡ በኪራሙ ወረዳ በሚኖሩ ነዋሪዎች ላይ ታጣቂዎች ጥቃት ማድረሳቸው ይታወቃል።

በነሐሴ 25/2016 ዓ.ም በወረዳው በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉንና አንድ ሰው መቁሰሉን መዘገባችን ይታወሳል።

አቶ ግርማ ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቁት በዚህ ጥቃት ሰለባ ከሆኑት መካከል አንዱ ዕድሜያቸው 40 ዓመት የሞላቸውና የሰባት ልጆች አባት የሆኑት አቶ በላቸው ዳንዮ በአሁኑ (በመስከረም 4/2017ዓ.ም. በተፈፀመው) ጥቃት የተገደሉት የሲሬ ዶሮ አስተዳደር ሃላፊ አላሚሮ ረታ የቅርብ ዘመድ እንደነበሩ ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ በኪራሙ ወረዳ ከሰኔ 12 እስከ 22 ባለው ጊዜ በደረሰ ሌላ ጥቃት ከአስራ አንድ በላይ ሰዎች ተገድለዋል።

አዲስ ስታንዳርድ የምስራቅ ወለጋ ዞን የፖሊስ ኃላፊ የሆኑትን ኮማንደር ዘላለም ነሞምሳን ለማግኘት ያደረገው ጥረት አልተሳካም። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button