ቢዝነስዜና

ዜና፡ በአማራ ክልል በተፈጠረው የሰላም እጦት ምክናያት በሩብ አመቱ 6 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር ብቻ ግብር መሰብሰቡ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 20/2016 .ም፡ በአማራ ክልል በዘንድሮ በጀት አመት 71 ነጥብ 61 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ወደ ስራ የገባ ቢሆንም በክልሉ በተፈጠረው የጸጥታ እና የሰላም ችግር ሳቢያ መሰብሰብ የቻለው 6 ቢሊዮን 264 ሚሊየን ብቻ መሆኑን አስታወቀ።

አብዛኛዎቹ የክልሉ ዞኖች እና ከተማ አስተዳደሮች የሚጠበቅባቸውን ገቢ በመሰብሰብ ረገድ አሳሳቢ ደረጃ ላይ የሚገኙ በመሆናቸው ትኩረት ሰጥተው መስራት እንዳለባቸው የክልሉ የገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፍቅረማሪያም ማሳሰባቸውን ከክልሉ ኮሙዩኒኬሽን ቢሮ የፌስቢክ ማህበራዊ ትስስር ገጽ ላይ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ገቢ ከሌለ የህክምና ተቋማት እና ት/ቤቶች ይዘጋሉ፤ የመንግስት ሠራተኞች ደመወዝ ይቆማል፤ ልማት እድገት፣ ብልጽግና አይኖርም ሲሉ በሩብ አመቱ ክልሉ የሰበሰበው ገቢ ማነስ ጋር በተያያዘ የክልሉ የገቢዎች ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ፍቅረማሪያም ደጀኔ መናገራቸውንም መረጃው አካቷል።

በ2016 በጀት ዓመት 71 ነጥብ 61 ቢሊዮን ብር ለመሰብሰብ ታቅዶ ሥራ የተጀመረ ቢሆንም በክልሉ የተፈጠረው የሠላም ዕጦት እና የቁረጥ ግብር ጥናቱ በወሰደው ጊዜ ምክንያት የታሰበው ገቢ ሊሰበሰብ አልቻለም ያለው መረጃው በዚህም በሩብ ዓመቱ 6 ቢሊዮን 264 ሚሊየን 985 ሺህ 447 ብር ወይም የዕቅዱን 34 በመቶ ብቻ መሰብሰብ መቻሉን አመላክቷል፡፡

ይህም ከባለፈው ተመሳሳይ በጀት ዓመት ጋር ሲነፃፀር በ2 ቢሊየን 140 ሚሊየን 398 ሺህ 891 ብር ያነሰ መሆኑን ጠቁሟል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button