ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና፡ በአማራ ክልል የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ታራሚዎች በይቅርታ እንዲለቀቁ ተወሰነ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 24/2016 .ም፡ የአማራ ክልል የይቅርታ ቦርድ የገናን በዓል ምክንያት በማድረግ ሁለት ሺህ 741 ታራሚዎች በይቅርታ እንዲፈቱ መወሰኑን የክልሉ ፍትህ ቢሮ ሃላፊ አቶ ብርሃኑ ጎሽም አሰታወቁ።

ቦርዱ ቀደም ሲል በይቅርታ ከማረሚያ ቤት ወጥተው የነበሩና 3 ዓመት ሳይሞላቸው ሌላ ወንጀል ፈጽመዋል የተባሉ 38 ግለሰቦች የተሰጣቸው ይቅርታ ተነስቶ በህግ እንዲጠየቁ መወሰኑም ተመልክቷል።

ቦርዱ ይቅርታውን ማድረግ የቻለው በቆይታቸው የባህሪ ለውጥ ያመጡና የቆይታ ጊዜያቸውን በአብዛኛው ማጠናቀቃቸውን በማረጋገጥ መሆኑን የቢሮ ሃላፊው አቶ ብርሃኑ ጎሽም ዛሬ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል ያለው የኢዜአ ዘገባ በይቅርታውም በሽብርተኝነት፣ በአስገድዶ መድፈር፣ በሙስና፣ በህገ ወጥ የሰዎች ዝውውርና በመሰረተ ልማት ማውደም ተከሰው የተፈረደባቸውን እንደማያካትት መግለጻቸውን አስታውቋል።

ከዚህ ቀደም ወንጀል ፈጽመው የነበሩና በይቅርታ የተለቀቁ ግለሰቦች ሶስት ዓመት ሳይሞላቸው ሌላ ወንጀል በመፈጸማቸው የተሰጣቸው ይቅርታ ተነስቶ በህግ እንዲጠየቁ መወሰኑንም አመልክተዋል።

ቦርዱ የሰጠው ይቅርታም ከታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ማረሚያ ቤቶች በሚደርሳቸው ደብዳቤ መሰረት ተፈፃሚ እንደሚሆን አስታውቀዋል።

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button