ማህበራዊ ጉዳይዜና
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስምጥ ሸለቆ የሚገኘው የሌጲስ መንደር በዓለም ድንቅ የቱሪዝም መንደርነት የእውቅና ሽልማት ማግኘቱ ተነገረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8/2016 .ም፡ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ አርሲ ዞን ነገሌ ከተማ የሚገኘው የሌጲስ ኢኮ ቱሪዝም መንደር በዓለም ድንቅ የቱሪዝም መንደርነት የእውቅና ሽልማት ማግኘቱን የቱሪዝም ሚኒስቴር በይፋዊ የፌስቡክ ገጹ አስታወቀ። በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኘው የሌጲስ መንደር የእውቅና ሽልማት ያገኘው ከተባበሩት መንግስታት የዓለም ቱሪዝም ድርጅት መሆኑን ሚኒስቴሩ ገልጿል።

አስደናቂ መልካአ ምድሮችን፣ ፏፏቴ፣ አእዋፋት እና የተለያዩ የዱር እንስሳት በውስጡ የያዘው የሌጲስ መንደር ከቀርከሃ በሚሰሩ የእደ-ጥበብ ውጤቶች በስፋት እንደሚታወቅ አመላክቷል።

ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም በዓለም ድንቅ መንደርነት የጮቄ ተራራ እና ከወንጪ የኢኮቱሪዝም መንደርን ማስመዝገቧን ያወሳው የሚኒስቴር መስሪያቤቱ መረጃ የሌጲስ መንደር ሶስተኛ ድንቅ የቱሪዝም መንደርነት ሆኖ መመዝገቡን አመላክቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button