ዜና

ዜና፡ አምባሳደር መለስ አለም ኢትዮጵያ ለአንዲት ቻይና ፖሊሲ ያላትን ቁርጠኝነት አርጋገጡ

አዲስ አበባ፣ ጥር 6፣ 2016 ዓ/ም፡_ የውጭ ጉዳይ ሚስኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ ዓለም (ዶ/ር) ኢትዮጵያ ለአንዲት ቻይና ፖሊሲ ያላትን ቁርጠኝነት አርጋገጡ።

ቃል አቀባዩ ከኢዜአ ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ ኢትዮጵያ ለአንዲት ቻይና ፖሊሲ  ኢትዮጵያ የአንዲት ቻይና ፖሊሲን ለረጅም ዓመታት ስታራምድ መቆየቷን እና የአንድ ቻይና ፖሊሲ አቋም በዘመናት መካከል መንግስታት አፅንተው የያዙት አቋም መሆኑን ገልጸዋል።

በመሆኑም “ኢትዮጵያ የአንድ ቻይና ፖሊሲ ላይ ያላት አቋም ዛሬም የጸና” መሆኑን አምባሳደር መለስ ተናግረዋል።

አምባሳደሩ ይህን ያሉት፤ ኢትዮጵያ እና ሶማሊ ላንድ የተፈራረሙትን የመግባቢያ ሰነድን በተመለከተ ቻይና የሶማሊያን ሉዓላዊነት እና የገዛት አንደነትን እንደምትደግፍ የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ መግለጻቸውን ተከትሎ ነው።  

ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ እና የሶማሊ ላንዱ ፕሬዝዳንት ሙሴ ባሂ አብዲ፤ ኢትዮጵያ የባህር በር እና የባህር ኃይል ቤዝ ለመገንባት የሚያስችላትን 20 ኪሎ ሜትር የባህር በር የምታገኝበትን የመግባቢያ ስምምነት መፈራረማቸው ይታወቃል። በስምምነቱ መሰረት ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ እውቅና የምትሰጥ ሲሆን መንግስት እውቅናውን የሚሰጠው ሁኔታውን በጥልቀት ካጤነ በኋላ መሆኑን ገልጿል

የቻይና የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማኦ ኒንግ የሶማሊያን ሉአላዊነት እና የግዛት አንድነቷን ለማሰጠበቅ ደጋፋቸውን ገልጸዋል። 

ቃል አቀባዩዋ ቻይና “ሶማሊ ላንድ የሶማሊያ አካል ናት” ብላ እንደምታምን በመግለጸ የቀጠናው ሀገራት የጋራ ልማት እና የወዳጅነት ትብብርን ለማስፈን የቀጠናውን ጉዳዮች በዲፕሎማሲያዊ ውይይት እንዲፈቱም ጥሪ አቅርባለች። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በምላሹ ባውጣው መግለጫ ሶማሊያ ለአንድ ቻይና ፖሊሲ ያላትን ቁርጠኝነት አርጋግጧል። “ ሶማሊያ ታይዋን የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ አካል መሆኗን ታሳወቃለች” ሲል መግለጫው ገልጿል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button