ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና፡ ኢትዮጵያ ከ168 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ስደተኞች የትምህርት እድል ሰጥቻለሁ ስትል ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ህዳር 15/2016 ዓ.ም፡- ከ168 ሺህ በላይ ስደተኞች በኢትዮጵያ የትምህርት እድል እንዲያገኙ መደረጉን ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ ሲል የኢፕድ ዘግቧል።

ትምህርት ሚኒስቴር ከግብረ-ሰናይና ልማታዊ ድርጅቶች ጋር በመተባበር 168 ሺህ 269 የሚሆኑ ስደተኞች የትምህርት እድል እንዲያገኙ አድርጓል ሲሉ በሚኒስቴሩ የስደተኛ ትምህርት መርሃ-ግብር ከፍተኛ የኮሚዩኒኬሽን ባለሙያ ዶ/ር እንግሊዝ ከተማ መናገራቸውን ዘገባው አስታውቋል።

ስደተኞቹ በ65 ቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች፣ በ53 አንደኛ ደረጃ እና በ11 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የትምህርት እድል እንዲያገኙ መደረጉን ያመላከተው ዘገባው በአቅራቢያቸው በሚገኙት የመንግሥት ትምህርት ቤቶች ከአካባቢው ማህበረሰብ ልጆች ጋር ተቀላቅለው እየተማሩ እንደሚገኙም ጠቁሟል።

ለስደተኞቹ ይህ የትምህርት እድል የተሰጠው በስንት አመታት ውስጥ መሆኑን ዘገባው አልጠቀሰም።

በተመሳሳይ የማህበረሰቡ ልጆችም ለስደተኞች ተብሎ የተሠሩት ትምህርት ቤቶች ውስጥ ከስደተኞች ጋር ተቀላቅለው እንዲማሩ እድሉ መመቻቸቱን እና ይህም ቋንቋ፣ ባህል እና አብሮነትን እንዲለማመዱ እድል እንደፈጠረላቸው አስታውቋል።

12ኛ ክፍልን አጠናቀው መግቢያ ነጥብ ያገኙ ተማሪዎች እንደማንኛውም ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ ምደባ እንደሚሰጣቸው እና በርካቶች አሁን ላይ በዩኒቨርሲቲ ገብተው እየተማሩ እንደሚገኙ ጠቁሟል።

በዋናነት ስደተኞቹ በጋምቤላ፣ በሱማሌ፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በአማራና በትግራይ ክልሎች እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሥር የተጠለሉ መሆናቸውንም አመላክቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ኢትዮጵያ ካስጠለለቻቸው ስደተኞች ግማሽ የሚሆኑት እድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ቢሆኑም ቀላል ቁጥር የማይባሉ በራሳቸውና በተለያዩ ምክንያቶች ወደ ትምህርት ቤት ሊመጡ አልቻሉም ብሏል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button