ቢዝነስ

ዜና: ለብሔራዊ ባንክ በዘጠኝ ወራት የቀረበው የወርቅ መጠን ሶስት ቶን ብቻ መሆኑ ተገለጸ፣ የተገኘው ገቢም 274 ሚሊዮን ዶላር ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 22/2016 ዓ.ም፡-የማዕድን ሚኒስቴር በዘጠኝ ወራት በኩባንያዎች አማካኝነት 2 ነጥብ 414 ቶን እንዲሁም በባህላዊ 0 ነጥብ 609 ቶን በአጠቃሊይ 3 ነጥብ 023 ቶን ወርቅ ለብሔራዊ ባንክ መቅረቡን እና 274 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ መገኘቱን አስታወቀ።

ይህም ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር በመጠን 12 ነጥብ 6 በመቶ እንዲሁም በገቢ 83 በመቶ ብልጫ አሳይቷል ብሏል።

ሚኒስቴሩ ይህንን ያስታወቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ግንቦት 22 ቀን 2016 ዓ.ም ባካሄደው 29ኛ መደበኛ ስብሰባው የማዕድን ሚኒስቴርን የ2016 በጀት ዓመት የ9 ወራት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባዳመጠበት ወቅት ነው።

ሪፖርተር ጋዜጣ ባስነበበው ዘገባ በመጋቢት ወር ብሔራዊ ባንክ የገባው ወርቅ 350 ኪሎ ግራም መሆኑን ጠቁሞ ይህም በ2014 ዓ.ም. መጋቢት ወር ከተገኘው 800 ኪሎ ግራም በእጅጉ ያነሰ እንደሆነ አመላክቷል።

በአገሪቱ ያሉ ወርቅ አምራቾች የባህላዊና የኩባንያ ተብለው ሲከፈሉ፣ በተለይ በባህላዊ አምራቾች የሚወጣው ወርቅ ሙሉ ለሙሉ በሚባል ደረጃ ወደ ብሔራዊ ባንክ መግባት ያቆመ መሆኑን፣ ባለፉት ዘጠኝ ወራት ከታቀደው 2‚306 ኪሎ ግራም ውስጥ 609 ኪሎ ብቻ (26 በመቶ) መቅረቡን መረዳት ተችሏል፡፡

አዳዲስ አራት የወርቅ ፋብሪካዎች ለማስፋፋት እየተሰራ መሆኑን ሪፖርቱን ያቀረቡት ሚኒስትሩ ኢንጂነር ሀብታሙ ተገኝ አስታውቀው ሁለቱ ወርቅ ማምረት መጀመራቸውን እና የቀሩት ደግሞ በቅርቡ ወደ ስራ እንደሚገቡ ገልጸዋል።

ሚኒስትሩ እንጂነር ሀብታሙ ተገኝ በኢትዮጵያ የማዕድን ዘርፉ ተስፋ ሰጪ ውጤት ማስመዝገብ በመቻሉ የሀገሪቱን ገቢ ለማሳደግ በሚደረገው ርብርብ የበኩሉን ሚና እየተወጣ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የማዕድን ዘርፉ በወርቅ፣ በድንጋይ ከሰል፣ በሲሚንቶ ምርትና ግብይት የተሻለ አፈጻጸም የታየበት መሆኑን አመላክተዋል።

በዘርፉ የህገ ወጥ ንግድን በመከላከል ረገድ ሰፊ ስራ መሠራቱን የገለፁት ሚንስትሩ፤ በህገ-ወጦች ላይም ተገቢነት ያለው እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል።

የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ከውጭ ሀገራት የሚያስገቡትን የድንጋይ ከሰል በአገር ውስጥ ምርት ለመተካት እና አቅርቦትን ለመጨመር አስቻይ ስትራቴጂ መዘጋጀቱን አስረድተዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button