ዜና

ዜና፡ ቅዱስ ሲኖዶሱ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ላይ ቅሬታ ማሰማቱን ተከትሎ ኮሚሽኑ ከሲኖዱሱ ጋር ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 30/ 2016 ዓ/ም፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ በሀገራዊ ምክክር ቤተክርስቲያኗ እንድትሳተፍ ጥሪ ባለመቅረቡ ቅሬታ ማሰማቱን ተከትሎ ኮሚሽኑ የሲኖዱሱ ጽ/ቤት ድረስ በመሄድ ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን አስታወቀ። 

ቅዱስ ሲኖዶሱ ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ሲያካሄድ የቆየውን የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ማጥናቀቁን ተከትሎ ትላንት ባወጣው መግለጫ ቤተክርስቲያኒቱ በኮሚሽኑ በኩል በይፋ የቀረበ የተሳትፎ ጥሪ እንዳልተደረገላት በመግለጽ በሂደቱ ቅር መሰኘቷን አስታውቋል።

ሲኖዶሱ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ መሰየሙንም አስታውቋል። 

ይህን ተከትሎ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በሰጠው መግለጫ፤ ኮሚሽኑ ገና ሥራውን እንደጀመረ የመግባቢያ ሠነድ የተፈራረመው ከአምስቱ ተባባሪ አካላት አንዱ ከሆነው ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር ነው ብሏል። ኮሚሽኑ እራሱን ከህዝቡ ጋር ሲያስተዋውቅ ቤተክርስቲያኒቱን በመወከል በየወረዳው፣ በዞንና በክልሎች በተካሄዱ መርሐግብሮች በሙሉ በጸሎትና ቡራኬ መስጠታቸውን ገልጿል።

የሲኖዶሱን ውሳኔ በአክብሮት የምንመለከተው ጉዳይ ነው ሲል የገለጸው ኮሚሽኑ አክሎም ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዱሱ ጽ/ቤት ድረሰ በመገኘት ለመወያየት ዝግጁ መሆኑን አረጋግጧል። ይህ የአካታችነት መርህ ከሁሉም የሃይማኖት ተቋማት ጋር በእኩልነት የሚተገበር መሆኑንም አስታውቋል።

ከበርካታ አካላት የገለልተኝነት እና አካታችነት ጥያቄዎች እየቀረቡበት ያለው ኮሚሽኑ በአዲስ አበባ አጀንታ የማሰባሰብ ሂደቱን አጠናቋል።  ሂደቱ ከሀገሪቱ ዋና ዋና የፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ ትችት እና ተቃውሞም ገጥሞታል። 

ከኮሚሽኑ ምስረታ ጀምሮ ቅሬታ ሲያሰሙ የቆዩ በኦሮሚያ ክልል ዋና የሚባሉት ፓርቲዎች ማለትም የኦሮሞ ፌዴራሊስት ፓርቲ (ኦፌኮ) እና የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ( ኦነግ) እራሳቸውን ከተሳትፎ ለይተዋል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ባለፈው ሳምንት አስራ አንድ ተቃዋሚ ፓርቲዎችን ያቀፈው የተቃዋሚ ፓርቲዎች ካውከስ ኮሚሽኑ “አካታች የሆነ አገራዊ ውይይትን የማሳለጥ አላማ አንግቦ ቢመሰረትም አላሳካም” ሲል ተችቷል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button