ዜና

ዜና፡ ቤተ ክርስቲያኗ በሀገራዊ ምክክር እንድትሳተፍ ኮሚሽኑ ጥሪ ባለማቀረቡ ቅዱስ ሲኖዶሱ ቅር መሰኘቱን ገለጸ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29/ 2016 ዓ/ም፦ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን እንድትሳተፍ ጥሪ ባለማቀረቡ ቅዱስ ሲኖዶሱ ቅር መሰኘቱን ገለጸ። ሲኖዶሱ የቤተ ክርስቲያኒቱ ተሳትፎና አጀንዳ የማቅረብ መብቷ እንዲረጋገጥ ከኮሚሽኑ ጋር በመነጋገር ጉዳዩን ተከታትሎ ለፍጻሜ የሚያበቃ ኮሚቴ መሰየሙንም አስታውቋል።  

ሲኖዶሱ ይህን የገለጸው ከግንቦት 21 እስከ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ/ም ድረስ ሲያካሄድ የቆየውን የርክበ ካህናት መደበኛ ስብሰባውን ማጥናቀቁን ተከትሎ ዘሬ ባወጣው መግለጫ ነው።

ምልዓተ ጉባኤው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንና በመንግሥት መካከል ሊኖር ስለሚገባው የሥራ ግንኙነት በቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት ከመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር የሚመካከር የብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት ልዑክ ቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙ ተገልጿል።

በመላ ሀገሪቱ በተፈጠሩ ግጭቶች፣ አለመግባባቶችና የሰላም ዕጦት በርካታ የሰው ሕይወት መጥፋትና የንብረት ውድመት መቀጠሉ እንዳሳዘነው የገለጸው ሲኖዶሱ ስለዚህ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሁሉም ባለድርሻ አካላት ከግጭትና ከጥፋት ድርጊት እንዲቆጠቡና  ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ጥሪ አቅርቧል።

የተመሳሳይ ጾታ ጋብቻና የግብረ ሰዶማዊነትን በሕገ ተፈጥሮም ሆነ በሰው ልጅ የሰብዓዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው በሆኑን በመግለጽ አውግዟል። ሲኖዶሱ የቤተ ክርስቲያንን አቋም በሚገልጽ መልኩ ራሱን ችሎ ዓለም አቀፋዊ ይዘቱን ባገናዘበ ሁኔታ ዝርዝር መግለጫ እንዲሰጥ ቅዱስ ሲኖዶስ ወስኗል። 

የቤተክረቲያኗ ፓትሪያርክ አቡነ ማቲያስ ግንቦት 21 ቀን 2016 በርክበ ካህናት የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤ ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ “የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ጊዜ በከባድ ፈተና ውስጥ እያለፈች ትገኛለች” ሲሉ ገለጸዋል። 

“ቤተክርስቲያኗ በውጭውና በውስጥ ፈተና ተልእኮዋን በአግባቡ እንዳትወጣ ዕንቅፋት ሆነውባታል” ያሉት ፓትሪያርኩ፤ “ፍቅረ ሢመትና ፍቅረ ንዋይ ነግሦአል፤ መለያየትና መነቃቀፍ እየሰፉ መጥተዋል” ሲሉም አክለዋል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

“ከኦርቶዶክሳዊ ቀኖና እና ሥርዓት ባፈነገጠ መልኩ ራስን በራስ የመሾም አባዜ እየተለማመዱ ነው” ያሉት አቡነ ማቲያስ ቤተ “ቤተክርስቲያናኗ በፈተና የማይናቅ ጉዳት እየደረሰባት ነው፤ ከሁሉ በላይ ደግሞ ሰላምዋና አንድነቷ ጥያቄ ላይ ወድቆአል” ማለታቸው ይታወሳል፡፡ አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button