ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሆነው ተሾሙ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 9/ 2016 ዓ/ም፦ የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ የምርጫ ጊዜ 3ኛ የስራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ ሾመ። 

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ጋትሏክ ሮንን (ዶ/ር) የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ መርጧል።

የአመራር ለውጥ ያስፈለገበት ምክንያት በክልሉ በሠላምና ፀጥታ እንዲሁም በልማት ዘርፍ በርካታ ስራዎች ቢሰሩም የተቀመጡ አቅጣጫዎች ውስንነቶች በመታየታቸው እና የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር ለሌላ የፓርቲ ተልዕኮ በመፈለጋቸው መሆኑ ተጠቁሟል።

በምክር ቤቱ የተሾሙት ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ቀደም ሲል በጋምቤላ ክልል የሴቶችና ህፃናት ቢሮ በኃላፊነት እንዲሁም በሌሎች ቢሮዎች በኃላፊነት አገልግለዋል።

ወደዛሬው ሹመት እስከመጡበት ድረስም በኢፌዴሪ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር የህፃናት ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ በመሆን ሲያገለግሉ ነበር።

አዲሷ ተሿሚ ወይዘሮ አለሚቱ ኡሞድ ክልሉን ከስድስት አመት በላይ ሲመሩ ከቆዩት ከአቶ ኡሞድ ኡጁሉ የርዕሰ መስተዳድር ስልጣናቸውን በይፋ ተረክበዋል።

የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ሆነት የተሾሙት ዶክተር ጋትሏክ ሮን፤ ከዚህ ቀደም የጋምቤላ ክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣በክልሉ ምክር ቤት የኢኮኖሚ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ፣ በጋምቤላ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንትነት እንዲሁም በጤና ሳይንስ ኮሌጅ ዲን ሆነው እንዳገለገሉ ተገልጿል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ወደዛሬው ሹመት እስከመጡበት ድረስም በኢፌዴሪ ውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር የሚኒስትሩ አማካሪ ሆነው እያገለገሉ እንደነበር ተጠቅሷል።

ዶክተር ጋትሏክ ሮን ክልሉን ከስድስት አመት በላይ በምክትል ርዕሰ መስተዳድርነት ሲያገለግሉ ከነበሩት ከአቶ ቴንኩዌይ ጆክ የምክትልነት ስልጣንን መረከባቸውን ከክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት የተገኘው መረጃ አመላክቷል።

ምክር ቤቱ የምክትል ርዕሰ መስተዳድሩን ሹመት በአንድ ተቃውሞ በአብላጫ ድምጽ ያፀደቀ ሲሆን በምክር ቤቱ ፊት ቃለ መሐላ ፈጽመዋል።

በክልሉ በተደጋጋሚ በሚቀሰቀሱ ግጭቶች ምክንያት ክልሉን ከስድስት አመት በላይ ሲመሩ ከቆዩት አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ከስልጣናቸው እንዲነሱ በበርካታ የክልሉ ነዋሪዎች ጥሪ ሲቀርብ ቆይቷል። በመጋቢት ወር በጋምቤላ ክልል በጆርና በኢታንግ ልዩ ወረዳ ተከስቶ ከነበረው የፀጥታ መደፍረስ ጋር በተያያዘ እጃቸው አለበት የተባሉ 14 አመራሮች በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል። ሌሎች ስምንት ሓላፊዎችም ክልሉ ሹመት መስጠቱ ይታወቃል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button