ዜናማህበራዊ ጉዳይህግ እና ፍትህ

ዜና፡ በሕገወጥ የማዕድን ዝውውር የተሳተፉ ከ100 በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ ርምጃ ተወሰደባቸው

አዲስ አበባ ህዳር 7/ 2015 ዓ/ም፦ በሕገወጥ የማዕድን ዝውውር የተሳተፉ ከ100 በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች ላይ የተለያየ ርምጃ መወሰዱን የማዕድን ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሕገወጥ የማዕድን ዝውውርን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ግብረ ኃይል በሕገወጥ የማዕድን ዝውውር የተሳተፉ ከ100 በላይ የውጭ ሀገር ዜጎች በሕግ እንዲጠየቁና በአስገዳጅ ሁኔታ ከሀገር እንዲወጡ መደረጉን የማዕድን ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ገልጸዋል፡፡

በተለያዩ የሀገሪቱ አካባቢዎች በሕገወጥ የማዕድን ማውጣትና ንግድ ተሠማርተው የነበሩ ከ100 በላይ የቻይና፣ የአፍሪካ ሀገራትና ከተለያዩ አህጉራት የመጡ ዜጎች ላይ ምርመራ በማድረግ ችግሩን ለመቀነስ ጥረት መደረጉን አመልክተዋል ሲል  ኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጀት ዘግቧል፡፡

ከቻይና ሀገር የመጡ ሕገወጥ ግለሰቦች በቤንሻጉል ጉሙዝ፤ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል እና በኦሮሚያ ክልል ጉጂ አካባቢ ሲንቀሳቀሱ እንደነበር አስረድተዋል።

የማዕድን ዘርፍ ለቀጣይ 10 ዓመታት ትኩረት ከተሰጣቸው ዘርፎች አንዱ እንደመሆኑ የተለያዩ የፖሊሲ ማሻሻያዎችና ዘርፉን የሚያሳድጉ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑን አስረድተዋል።

ከውጤት አንጻርም ከቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያና ጋምቤላ ክልል ወደ ብሔራዊ ባንክ የሚገባው የወርቅ መጠን ዕድገት ያሳየ ሲሆን፤ በኦሮሚያ ክልል ጉጂ አካባቢ ተጨማሪ ሥራ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

በትግራይ ክልልም ሰፊ የወርቅና የሌሎች ማዕድናት ክምችት መኖሩን ተከትሎ የማልማት ሥራ የሚሠራ ሲሆን፤ ግብረ ኃይሉ በትግራይ ክልል እንዲሠማራ ከክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ጋር ውይይት እየተደረገ እንደሚገኝ አመልክተዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ሚኒስትር ዴኤታው እንዳስታወቁት፤ በማዕድን ዘርፉ ያለውን ሕገወጥነት ለመቀነስ በርካታ ሥራዎች ቢከናወኑም አሁንም የቁጥጥር ሥራዎችን አጠናክሮ መቀጠል ይገባል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button