ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ማይክ ሀመር በቀጣይ አስር ቀናት በኢትዮጵያ፣ ጂቡቲ እና ኳታር ጉብኝት ያካሂዳሉ ተባለ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 28/2016 ዓ.ም፡- የአሜሪካ የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሀመር በጂቡቲ፣ ኳታር እና ኢትዮጵያ ለአስር ቀናት ጉብኝት እንደሚያካሂዱ ተገለጸ።

ማይክ ሀመር ከህዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 7 ቀን 2016 ዓ.ም በሶስቱ ሀገራት በሚያደርጉት ጉብኝት በዋናነት በሱዳን ጉዳይ ከየሀገራቱ ከፍተኛ ባለስልጣናት እና ከአፍሪካ ህብረት ጋር እንደሚመክሩ የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በድረገጹ ያጋራው መረጃ ያሳያል።

ማይክ ሀመር በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከሀገሪቱ ባለስልጣናት ጋር በፕሪቶርያው ስምምነት አተገባበር ዙሪያ እንደሚወያዩም መስሪያ ቤቱ ጠቁሟል። የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲተገበር ግፊት ያደርጋሉ ያለው መስሪያ ቤቱ በሽግግር ፍትሁ እና ተጠያቂነት ማስፈን እንዲሰፍን ይወያያሉ ብሏል። በአማራ እና ኦሮምያ ክልሎች በመካሄድ ላይ ያለውን ግጭት በሰላማዊ ድርድር መፍትሔ እንዲያገኝ ለማስቻል ጥርት እንደሚያደርጉም ጠቁሟል፤ ሁሉም አካላት ንጹሃንን ከጉዳት እንዲጠብቁ፣ ከጥላቻ ንግግር እንዲታቀቡ እና ሰብአዊ መብትን እንዲያከብሩ ግፊት ያደርጋሉ ብሏል።  

በጂቡቲ ቆይታቸው በሱዳን ወቅታዊ ጉዳይ በሚመክረው የኢጋድ 41ኛው ልዩ ስብሰባ ላይ እንደሚታደሙ ያስታወቀው የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በኳታር በሚኖራቸው ቆይታም በዶሃ ፎረም እንደሚታደሙ አመላክቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button