ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ሰራዊቱ በጥቃቅን ችግሮች እንዳይጠመድ የፖለቲካ አመራሩ የፖለቲካ ችግሮችን መፍታት አለበት ተባለ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 6/2016 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በጥቃቅን ችግሮች እንዳይጠመድ የፖለቲካ አመራሩ የፖለቲካ ችግሮችን መፍታት አለበት ሲሉ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የውጭ ግንኙነትና ሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዲማ ነጎ (ዶ/ር) መናገራቸው ተገለጸ።

ቋሚ ኮሚቴው የሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የ2016 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸምን መገምገሙን እና በወቅቱም የፖለቲካ አመራሩ የፖለቲካ ስራዎችን በመስራት ሠራዊቱ ከጥቃቅን የፀጥታ ችግሮች እንዲወጣ ማድረግ እንደሚገባው ዶ/ር ዲማ መናገራቸውን የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በይፋዊ የማህበራዊ ትስስር ፌስቡክ ገጹ ያጋራው መረጃ ያሳያል።

ሠራዊቱ የተሰጠውን ሀገራዊ ተልዕኮ በመወጣት ለሕገ-መንግስቱ ያለውን ታማኝነት በቀጣይ አጠናክሮ እንዲቀጥል ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በትኩረት መስራት እንዳለበት ተመላክቷል ያለው መረጃው ሠራዊቱ የሀገሪቷ የመጨረሻ ምሽግ መሆኑን ተረድቶ መንቀሳቀስ ይገባል መባሉንም አስታውቋል።

ኢትዮጵያ በሰላም ማስከበር ተልዕኮ ያላትን ከፍተኛ ሚና በማውሳትም ሠራዊቱ የተለመደውን ብቃቱን እንዲወጣ ለስምሪት የሚላኩ የሠራዊት አባላት ምልመላ አሠራር ግልፀኝነት እንዲኖረው መሰራት እንዳለበት መጠቆሙን አካቷል።

የመከላከያ ሚኒስትር አብርሃም በላይ (ዶ/ር) በበኩላቸው የቀበሌ፣ የወረዳና የዞን አስተዳደሮች የፀጥታ ስራቸውን በአግባቡ ባለመስራታቸው ሠራዊቱ በየሰፈሩ እና በየቀበሌው ለጥቃቅን ስራዎች እየተሰማራ ነው ሲሉ ለቋሚ ኮሚቴው መግለጻቸውነ መረጃው አስታውቋል።

ሠራዊቱ ለሀገሩ ሉዓላዊነት መከበር ትልቅ ዋጋ እየከፈለ መሆኑን ሚኒስትሩ ጠቅሰዋል ያለው መረጃው ይሁን እንጂ በጽንፈኛ ኃይሎች ያለ ስሙ ስም እየተሰጠው ከፍተኛ የስም ማጥፋት ዘመቻ ተከፍቶበታል ሲሉ ቅሬታቸውን ማሰማታቸውን አመላክቷል።

በየትኛውም የዓለም ክፍል የሀገሩን ሠራዊት ደፍሮ የሚሳደብና የሚያጥላላ አካል አለመኖሩርሃ ገልጸዋል ያለው የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በፌስቡክ ገጹ በሠራዊቱ ላይ የማጥላላትና የስድብ ዘመቻ በከፈቱ አካላት ላይ ተጠያቂነትን ማስፈን እንደሚገባ ማሳሰባቸውንም አካቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ሀገርን ለመበተን የሚሰሩ ኃይሎች በሠራዊቱ ላይ የከፈቱትን ማጥላላት ለመከላከል ሁሉም ዜጋ ከሠራዊቱ ጎን ሊሰለፍ እንደሚገባ ሚኒስትሩ ጥሪ ማቅረባቸውንም መረጃው አካቷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button