ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና፡ በሀገሪቱ እየተካሄደ ያለው ግጭት አስቸኳይ እንዲቆምና ሰላማዊ ድርድር እንዲደረግ ጤና ባለሙያዎች ማህበር ጥሪ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 19/ 2016 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ጤና ባለሙያዎች ማህበር በሀገሪቱ የተላያዩ አካባቢዎች በአሁኑ ወቅት በመካሄድ ላይ ያለው ግጭት በአስቸኳይ እንዲቆምና ሰላማዊ ድርድር እንዲደረግ ጥሪ አቀረበ፡፡

ማህበሩ አክሎም  በትግራይ ፣በኦሮሚያ ፣ አሁን ደግሞ በዋናነት በአማራ እና ሌሎች አንዳንድ ክልሎች የሚነሱ ግጭቶችና የእርስ በርስ ጦርነቶች ከጤና ቀዉስ አልፎ በከፍተኛ ደረጃ የሰዉን ህይወት እየቀጠፈ ይገኛል በማለት ትላንት መስከረም 18 ቀን ባወጣው መግለጫ ገልጧል፡፡ በዚህ ዉጤት አልባ ተግባር የጤና ባለሙያዎች እና ህዝባችን ላልተገባ ስቃይ እየዳረገ በመሆኑ ማህበሩ ይሄን ተግባር በጽኑ አወግዛለው ነው ያለው፡፡

በቅርቡ በአማራ ክልል በተከሰተዉ ግጭትና አለመረጋጋት በማህበረሰቡ ላይ ከፍተኛ የሆነ የጤና እክል አስከትሏል ያለው ማህበሩ “አንቡላንሶች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰዉ አገልግሎት አለመስጠት እና ከታለመላቸዉ አላማ ዉጭ ለወታደራዊ እንቅስቃሴ አገልግሎት ሲዉሉ ተስተዉሏል፡፡ አሁንም ወደ ጤና ተቋም አገልግሎት ያልተመለሱ ብዙ አንቡላንሶች እንዳሉ አረጋግጠናል” ሲል ገልጧል፡፡

በመሆኑም በጦርነቱ ወቅት አንቡላንሶችን ከታለመላቸዉ አላማ ዉጭ መጠቀም እንዲቆም እና አንቡላንሶች ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሰዉ የህይወት አድን ስራቸዉን መስራት ሚችሉበት ሁኔታ እንዲፈጠር ማህበሩ በአፅኖት አሳስቧል።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሃገሪቱ የሚስተዋሉ አለመረጋጋቶች እና ግጭቶች በጤና ስርዓቱ ላይ ከፍተኛ ስጋት መደቀናቸውን የጠቀሰው የጤና ባለሙያዎች ማህበር፣ የጤና ተቋማት የጦርነቱ ሰለባ ገፈት ቀማሽ በመሆናቸው ከደረሰባቸዉ ጉዳት በቅጡ እንኳ ሳያገግሙ እና በቂ ድጋፍ ሳይደረግላቸዉ አንዳንድ አካባቢዎች አሁንም የጉዳቱ ሰለባ እየሆኑ ይገኛሉ” ብሏል፡፡

ማህበሩ በትግራይ፣አፋርና አማራ ክልል በጦርነቱ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸዉ ጤና ተቋማት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ መልሶ የማቋቋም እና በሙሉ አቅማቸዉ ወደ አገልግሎት እንዲመለሱ ማድረግ ቀዳሚ የመንግስት ሃላፊነት ሊሆን ይገባልም አሳስቧል።

በተጨማሪም ማህበሩ በመግለጫው ጤና ባለሙያዎች ኑሮአቸውን ለመምራት የሚያስችል ደሞዝም ሆነ ጥቅማጥቅሞች ተነፍገዉ እየኖሩ በመሆኑ ለጠቅላይ ሚኒስቴር ፅፈት ቤት ጨምሮ ለሚመለከታቸው ለመንግስት አካላት በተደጋጋሚ የደሞዝና የመብት ጥያቄዎችን ብናቀርብም ምንም አይነት ምላሽ አልተሰጠም ሲል ቅሬታውን ገልጧል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በዚህም ሳቢያ የጤና ባለሙያዎች ለከፋ የኑሮ ቀዉስ ተዳርገዋል ያለው ማህበሩ የተነሱትን የመብት ጥያቄዎች አስቸኳይ መፍትሄ እንዲሰጣቸዉ ጠይቋል፡፡አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button