ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና፡ በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በተፈጸመ ጥቃት15 ሰዎች ተገደሉ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 9/ 2016 ዓ/ም፦ በኦሮሚያ ክልል ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን አቤ ዶንጎሮ ወረዳ ባሳለፍነው ሳምንት በታጣቂዎች በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ 15 ሰዎች መገደላቸውን የስፍራው ነዋሪዎች ገለጹ።

አቤ ዶንጎሮ ወረዳ ነዋሪ አብደታ ተስፋዬ ጥቃቱ ረቡዕ ነሃሴ 1 ቀን  ከጠዋቱ 2፡30 ገደማ ወደ ገበያ እየሄዱ ባሉ ሰዎች ላይ ሚርጋ በሚባል አካባቢ መፈጸሙን ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል።

“የፋኖ አባላት” መሆናቸው የተገለፀው ጥቃት አድራሾቹ አምስት ሰዎችን ገድለው ሌሎች ሁለት ሰዎችንም አቁስለዋል ሲል ነዋሪው ገልጿል። አክሎም ነጋዴዎቹ የተኩስ ልውውጡ እንደተነሳ ወዲያውኑ ከስፍራው ሸሽተዋል ብሏል።

በጥቃቱ ህይወታቸው ካለፈ ሰዎች መካክለ ሁለቱ ሃዊ ከበደ እና ውርቂኔ በየነ የተባሉ ሴቶች መሆናቸውን አብደታ ገልጿል። 

በተመሳሳይ ቀን በቸሩ ቀበሌ “የፋኖ አባላት እና የኦሮሚያ ፖሊስ የደንብ ልብስ የሚመስል የለበሱ ግለሰቦች” በፈጸሙት ጥቃት 8 ሰዎች መገደላቸውን ነዋሪው አክሎ ተናግሯል። 

የአቤ ዶንጎሮ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ ከተማ ዋቁማ፤ በቸሩ ቀበሌ ለተገደሉት 8 ሰዎች “ድንበር ተሻግረው የመጡ ጽንፈኛ የፋኖ አባላት” ያሏቸውን አካላት ተጠያቂ አድርገዋል። 

በጥቃቱ ሶስት ንጹሃን ሰዎችም መቁሰላቸውንና ወዲያው ወደ አቤ ደንጎሮ ሆስፒታል ለህክምና መወሰዳቸውን አስተዳዳሪው ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

“በቸሩ በተፈጸመው ጥቃት የመንግስት ሠራተኞ እንዲሁም ንጹሃን ሰዎች መሞታቸውን” አስረድተዋል። 

የፋኖ ታጣቂዎቹ በምስራቅ ወለጋ ዞን ጊዳ ወረዳ በኩል ወደ አቤ ዶንጎሮ ቀበሌ ዘልቀው እንደሚገቡ ነዋሪዎች ተናግረዋል።

“ጥቃቱን ተከትሎ ሰዎች ከአካባቢው እየሸሹ በአቤ ዶንጎሮ ወረዳ ውስጥ መጠለያ እየፈለጉ ነው። እነዚህ ተፈናቃዮች ለሰብዓዊ ቀውስ ተጋልጠዋል፤ ከአቤ ዶንጎሮ ከተማ እና ገራሮ ቀበሌ ድጋፍ እየተደረገላቸው ነው ” ብለዋል አቶ ከተማ። 

በሆሮ ወረዳ ሃሮ ሾቴ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑት አህመድ አሊ፤ “የፋኖ ታጣቂዎች” ነሃሴ 3 ቀን በቀበሌው ጥቃት መፈጸማቸውን ገልጸው ሁለት ሰዎች ተገድለዋል ብለዋል። በርካታ ሰዎች እስካሁን የደረሱበት አለመታወቁንም ገልጸዋል።

ነሐሴ 2 ቀን በሃናፋሬ ዳርጌ ቀበሌ ካታ በሚባል ቦታም “የፋኖ ታጣቂ ቡድን ወደ ሻምቡ ከተማ በሚወስደው መንግድ ሁለት አውቶቡሶች ላይ ጥቃት በመሰንዘር ተንቀሳቃሽ ስልኮችን፣ አልባሳትንና ገንዘብ ዘርፏል፤ ነገር ግን ምንም ዓይነት አካላዊ ጉዳት አላደረሱም” ሲሉ አህመድ ተናግረዋል።

በአዲስ ስታንዳርድ በቅርቡ በምዕራብ ኦሮሚያ በተለይም በሆሮ ጉዱሩ ወለጋ ዞን በመንግስት ኃይሎች፣ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊን እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል  በመካሄድ ላይ ባለው የትጥቅ ግጭት ምክንያት የፀጥታ ስጋት እየተባባሰ መምጣቱን ዘግቧልአስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button