ዜናህግ እና ፍትህ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በመቀሌ የተቃውሞ ሰልፍ ለመዘገብ በወጡ ሶስት ጋዜጠኞች ላይ ድብደባ እና እስራት ያደረሱ የፀጥታ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ሲፒጄ ጠየቀ

አዲስ አበባ፣ መስከረም 12/ 2016 ዓ.ም፡- ዓለም አቀፉ የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ ሲፒጄ በመቀሌ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ለመዘገብ በወጡት ተሸገር ፅጋብ፣ መሃሪ ካሰይ እና መሀሪ ሰለሞን የተባሉ የበይነ መረብ ጋዜጠኞች ላይ ድብደባ እና እስራት ያደረሱ የፀጥታ አካላት ተጠያቂ እንዲሆኑ ጠየቀ፡፡

ሲፒጄ ሃሙስ ባወጣው መግለጫ የየበለ ሚዲያ ዘጋቢ ተሸገር ፅጋብ፣ የኣያም ሚዲያ መስራች እና ዘጋቢ መሃሪ ካሰይ እና መሀሪ ሰለሞን በፀጥታ አካላት መታሰራቸውን ገልፆ “በህገ ወጥ ሰልፍ ላይ ተሳትፏችኋል” በሚል የታሰሩት መሃሪ ካሰይ እና መሀሪ ሰለሞን ነሃሴ 28 በዋስ ተፈተዋል ብሏል፡፡ ጋዜጠኛ ተሻገርም በቁጥጥር ስር የዋለበት ምክንያት ሳይነገረው መለቀቁን ሲፒጄ አስታውቋል፡፡

“በጋዜጠኞቹ ላይ የደረሰው ድብደባ እና እስራት የትግራይ ባለስልጣናት ወሳኝ የሆኑ ጉዳዮችን ጋዜጠኞች እንዲዘግቡ አለመፈለጋቸውን የሚያሳይ ነው፡፡ የክልሉ ግዚያዊ አስተዳደር በጋዜጠኞቹ ላይ የተፈጸመውን ድርጊት እንዲያጣራ እና የፀጥታ አካላቱን ተጠያቂነት ሊያረጋግጥ ይገባል፡፡ ሚዲያዎች የተቃውሞ ሰልፎችን መዘገብ እንዲችሉ ወስትና መስጠት አለበት” ሲሉ በምሥራቅ አፍሪካ የሲፒጄ ሃላፊ ሙቶኪ ሙሞ ተናግረዋል፡፡

በመቀሌ ከተማ ሊካሄድ በታቀደው የተቃውሞ ሰልፍ ላይ ሶስቱም ጋዜጠኞች በተናጥል እየቀረፁ ሳለ የፖሊስ አባላት እንዲያቆሙ በመንገር በጨፈቃ እና በኤልክትሪክ ገመድ ድብደባ አድርሰውባቸዋል ሲል ሲፒጄ በመግለጫው ገልጧል፡፡

ጋዜጠኛ ተሻገር ከፖሊሶቹ ለማምለጥ ባደረገው ጥረት በቅርቡ ወዳገኘው ካፌ ቢጋባም ፖሊሶቹ አግኝተውት እራሱን እስኪስት እንደደበደቡት እና ከዙያም በመቀሌ ከተማ ሰሜን ክፍለ ከተማ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰዱት ለተቋሙ ተናግሯል፡፡ ተሻገር ከድብደባው በኋላ የአይኑ እይታ መደብዘዙን እና ጭንቅላቱ ፣ጀርባው እና እግሮቹ መቁሰላቸውን ተናግሯል።

በተመሳሳይ መልኩ መሃሪ ሰለሞን እና መሃሪ ካሰይ ከፖሊሶቹ አምልጠው የነበር ሲሆን በማግስቱ ካፌ ቁርብ በመብላት ላይ ሳሉ በፖሊሶች ተይዘው እየተደበደቡ ወደ ፓትሮል ተሸከርካሪያቸው ለ 10 ደቂቃ በባዶ እግራቸው እንዲሄዱ በማድረግ ወደ ፖሊስ ጣቢያ እንደወሰዷቸው ገልፀዋል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ሲፒጄ፣ የክልሉ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ እና የኮሚዩኒኬሽን ጽ/ቤትን በጉዳዩ ዙሪያ ላቀረብኩላቸው ጥያቄ ምላሽ አልሰጡኝም ሲል አስታውቋል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button