ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በባቢሌ ወረዳ በተቀሰቀሰ ግጭት የበረካታ ሰዎች ህይወት አልፈ፣ በርካቶች ቆስለዋል

አዲስ አበባ፣ መስከረም 11/ 2016 ዓ.ም፡- ከ ኦሮሚያ እና ሶማሊ ክልል የተወጣጡ ታጣቂዎች መካከል በባቢሌ ወረዳ በተፈፀመ ግጭት በርካታ ንፁሃን ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን እና በርካቶች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገለፁ፡፡

በሶማሊ ክልል ፋፋን ዞን እና በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሀረርጌ ዞን አስተዳደር ስር በምትገኝው ባቢሌ ወረዳ፣ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ታጣቂ ሃይሎች በ2017 በነበረው ግጭት ከኦሮሚያ የተፈናቀሉ ከ20,000 በላይ የሶማሊ ተወላጆችን በያዘውና በሶማሊ ክልል በሚገኘው ኮሎጂ ካምፕ ላይ ሰኞ እለት ጥቃቅ ከፍተዋል ሲሉ ሁለት ከሶማሊ ወገን የሆኑ ምንጮች ለአዲስ ስታንዳርድ ተናግረዋል፡፡

ለሶስት ቀናት በዘለቀው ግጭቱ ሴቶች፣ ህፃናት እና አዛውንቶችን ጨምሮ የበርካታ ሰዎች ህይወት ማለፉን መረጃ ሰጪዎቹ ገልጸዋል። በጅግጅጋ ሆስፒታል የህክምና ባለሙያው ሞሃመደ ሰኢድ ከሰኞ ጀምሮ በነበረው ግጭት ህይወታቸው ካለፈ ቢያነስ አስር ሰዎች መካከል ሁለት ሴቶች እና ሶስት ህጻናት እንደሚገኙበት ገልፀው ጉዳት ከደረሰባው ከሃያ በላይ ከሚሆኑት ሰዎች ውስጥ ዘጠኙ ሴቶች እና እድሜያቸው ከ5 አመት በታች የሆኑ ህጻናት ናቸው ሲል ተናግረዋል፡፡

ከኦሮሚያ በኩል የባቢሌ ወረዳ ነዋሪ ለአዲስ ስታንዳርድ እንደተናገሩት ግን ኮሎጂ ካምፕ ተብሎ የሚጠራው ቦታ በኦሮሚያ ክልል አዋሳኝ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን የሶማሌ ክልል መንግስት በህገ-ወጥ መንገድ በአካባቢው ሰዎችን በማስፈር ቦታው የሶማሌ ክልል ስር እንዲሆን ጥረት አድርጓል።

ግጭቱ የተቀሰቀሰው የሶማሌ ክልል መንግስት በቅርቡ በአካባቢው የተከለውን የፍተሻ ቦታ የኦሮሚያ ሚሊሻዎች እንዲነሳ ከጠየቁ በኋላ ነው ሲል ገልጿል። ነዋሪው የኦሮሚያ ሚሊሻዎች በኮሎጂ ካምፕ ላይ ጥቃት ፈጽመዋል በሚል ከሶማሊ በኩል የተነሳውን አስታየት አጣጥሏል።

የአሁኑ ግጭት የ2004ቱን ህዝበ ውሳኔ ተከትሎ በአካባቢው ያለው የአስተዳደር ወሰን በግልፅ የተከለለ በመሆኑ ከይገባኛል ጥያቄ ጋር በተያያዘም ሆነ በሁለቱ ክልል ነዋሪዎች መካከል የተፈጠረ አለመሆኑን ለሶማሌ ክልል አስተዳደር ቅርበት ያለው ምንጭ ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጿል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ከሁለቱም ወገኖች በግጭቱ ንፁሃን ሰዎች መገደላቸውን የገለጸው ምንጩ፣ በኮንትሮባንድ ንግድ በተለይም የጫት ንግድ ላይ ፍላጎት ያላቸው ሰዎች የመንግስት ሚሊሻዎችን ተጠቅመው ግጭቱን እንደጀመሩ ገልጾ፣ በቅርቡ በአካባቢው የሶማሌ ክልል ምንግስት የፍተሸ ቦታ ማቆሙን ገልጿል።

የፌደራል መንግስት ሃይሎች እስካሁን ድረስ ጣልቃ እንዳልገቡ የገለጹት ምንጩ፣ የሁለቱ ክልል ፕሬዝዳንቶችን ጨምሮ ሌሎች ኃላፊዎች በአዳማ ከተማ እየተካሄደ ባለው የገዢው ብልፅግና ፓርቲ ስልጠና ላይ እየተሳተፉ በመሆኑ በጉዳዩ ላይ እንደሚወያዩ ተስፋ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል፡፡

ለተጨማሪ መረጃ የባቢሌ ወረዳ እንዲሁም የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ኃላፊዎችን አስተያየት ለማካተት አዲስ ስታንዳርድ ያደረገው ሙከራዎች አልተሳካም፡፡

በመጋቢት ወር አዲስ ስታንዳርድ በሶማሌ ክልል ቱሉ ጉሌድ ወረዳዎች እና በኦሮሚያ ክልል ጭናቅሳን አጎራባች በሚኖሩ ማህበረሰቦች መካከል ለቀናት በዘለቀ ግጭት ሰባት ሰዎች መገደላቸው እና 14 ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸውን ዘግቧል።

በጥር ወር በኦሮሚያ ክልል መንግስት የታዘዙ ሰራተኞች በሶማሌ ክልል በፋፋን ዞን ቱሉ ጉሌድ ወረዳ በማራር ቀበሌ የግድብ ግንባታ ሲጀምሩ በተፈጠረ ግጭት ቢያንስ 3 ንፁሀን ዜጎች ሲገደሉ 12 ሰዎች ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button