ዜናፖለቲካማህበራዊ ጉዳይ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ቀውስና የጾታዊ ጥቃቶች ተጽዕኖ እንዳሳሰቡት ሪፊውጂ ኢንተርናሽናል አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 18/ 2016 ዓ/ም፦ በትግራይ ክልል ሰብዓዊ ቀውስ እና ከግጭት ጋር ተያያዥ በሆኑ የጾታዊ ጥቃቶች ተጽዕኖ እንዳሳሰቡት ሪፊውጂ ኢንተርናሽናል የተሰኘ ግብረ ስናይ ድርጅት አስታወቀ:: 

ሪፊውጂ ኢንተርናሽናል በትግራይ ክልል ያለውን ሰብዓዊ ቀውስ በተመለከተ ትላንት ባወጣው መግለጫ የድርጅቱ ከፍተኛ ባለሙያ ሳራ ሚለር በትግራይ ክልል ጉብኝት ማድረጋቸውን ገልጾ በክልሉ ሲካሄድ የቆየው ጦርነት ቢያበቃም ህዝቡ በከባድ የሰብአዊ ቀውስ ውስጥ ይገኛል ብሏል፡፡ 

ድርጅቱ መጠነ ሰፊ ሰብአዊ ቀውስ፣ የአለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች ጥረት ማነስ እና ከግጭት ጋር በተያያዙ ጾታዊ ጥቃቶች የተጋለጡ ሴቶች ጉዳይ አሳሳቢ መሆኑን በቅርቡ በትግራይ ባደረኩት ጉብኝት ተረድቻለው ሲል ገልጿል። 

“በመላው ትግራይ ያሉ ሴቶች እና ልጃገረዶች ችግር አስደንጋጭ ነው። እ.ኤ.አ. በ2021 እና በ2022 በትግራይ፣ በኢትዮጵያ መንግስት፣ በአማራ እና በኤርትራ ኃይሎች መካከል በተደረገው ጦርነት በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተገድለዋል። በሁሉም እድሜ ያሉ ሴቶች በታጠቁ አካላት ተደፈረዋል፤ አንዳንዶቹ በቤተሰብ አባላት ፊት ድርጊቱ ተፍጽሞባቸዋል። ሌሎች ደግሞ በሌላ ፆታዊ ጥቃት አይነት ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል።” ሲሉ የድርጅቱ ባለሙያ ሳራ ሚለር ተናግረዋል፡፡

“በርካታ የትግራይ ሴቶች ለአካላዊ እና ስነ-ልቦናዊ ጉዳት ተዳርገዋል” ያሉት ባለሙያዋ  ቁጥሩን በትክክል ማወቅ አስቸጋሪ ቢሆንም በጤና ባለሙያዎች ግምት ከ40 እስከ 50 በመቶ የሚሆኑት ሴቶች ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች ደርሶባቸዋል ብለዋል። ከዚህ ውስጥ 80 በመቶ በላይ የሚሆኑ ሴቶች የተደፈሩት ሲሆን 70 በመቶው የሚሆኑት በቡድን የተደፈሩ ናቸው ሲሉ አክለው አስታውቃዋል። 

በድርጅቱ መግለጫ ከግጭት ጋር በተያያዙ ጾታዊ ጥቃቶች ሰለባ የነብሩ ሴቶች ተፈናቀለው እንደሚገኙ እና በአንዳንድ አካባቢዎች ባለው የጸጥታ ችግር፣ እንዲሁም እንድ ክሊኒኮች እና ትምህርት ቤቶች ያሉ የመሠረተ ልማቶች መውደም የተነሳ ወደ ቀያቸው መመለስ አልቻሉም ነው የተባለው። ሰፍረው በሚገኙበት ካምፕ የምግብ፣ የውሃ፣ የንጽህና በጠበቂያ ቁሶች እና ህክምና እጥረት መኖሩንም አመላክቷል፡፡

ሪፊውጂ ኢንተርናሽናል የአሜሪካው ተራዳኦ ድርጅት ዪኤስአይዲ በክልሉ የምግብ እርዳታን በማቆሙ ረሃብ መስፋፋቱን ግልጿል፡፡ በክልሉ ያሉ ሴቶች አስቸኳይ እርዳታን ይሻሉ ያሉት ሳራ ሚለር የስነ ልቦና ድጋፍ በአስቸኳይ ቅድሚያ ሊሰጠው የሚገባ ጉዳይ ነው በለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ይህ በእንዲህ እያል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በትግራይ የሰብአዊ መብቶች ሁኔታ ክትትል ግኝቶች ዙሪያ ቅዳሚ ባውጣው መግለጫ ከጾታዊ እና ወሲባዊ ጥቃት ጋር በተያያዘ በክልሉ እየተሰጠ ያለው አገልግሎት ከተፈጸመው ጥቃት አኳያ የማይመጣጠን መሆኑን አስታውቋል፡፡  ኢሰመኮ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች የሚሰጥ ማኅበራዊ፣ ሥነ ልቦናዊ እና ኢኮኖሚያዊ እገዛ ዝቅተኛ መሆኑ እና የለጋሽ ድርጅቶች ያልተቀናጀ ድጋፍ መስጠት በአሳሳቢነት ተለይተዋል በሏል።

የጾታዊ ጥቃት ተጎጂዎች አገልግሎትን አስመልክቶ በጤና ቢሮ አስተባባሪነት የባለድረሻ አካላት ሚና እና ኃላፊነት የሚያሳይ ዝርዝር መመሪያ መዘጋጀቱን፣ ከለጋሽ ድርጅቶች ጋር በመተባበር ለሰባት የአንድ መስኮት አገልግሎት መስጫ ማእከላት እና ለሁለት የተሐድሶ ማእከላት አልትራሳውንድ መሰጠቱ እና የምርመራ አገልግሎት መጀመር መቻሉን ተገልጿል ነው የተባለው። የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ አመራር የሆኑት ዶ/ር ስምዖን ገ/ጻድቕ ጾታዊ እና ወሲባዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሴቶች የሚሰጠው አገልግሎት በጤና ተቋማት ላይ በደረሰ ጉዳት የተነሳ ውስን መሆኑን አስረድተዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button