ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በትግራይ የታወጀው የሀዘን ቀን መከበር ጀመረ፣ ለሶስት ቀናት ይቀጥላል

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 3/2016 .ም፡ በትግራይ ሀይሎች እና በፌደራል መንግስቱ መካከል ተካሂዶ በነበረው ደም አፋሳሽ ጦርነት ወቅት ህይወታቸው ያለፉ ተዋጊዎችን ለመዘከር ከዛሬ ጥቅምት 3 ቀን ጀምሮ ለሶስት ተከታታይ ቀናት ክልላዊ የሀዘን ቀን በሁሉም የክልሉ ከተሞች መከበር ተጀምሯል።

ለሰማዕታቱ ቤተሰቦች መርዶ በይፋ መንገር ትላንት መጀመሩ የተገለጸ ሲሆን በተለያዩ የክልሉ ከተሞች በተለያዩ ስነስርአቶች የሀዘን ቀኑ መጀመሩን የክልሉ መገናኛ ብዙሃን አስታውቀዋል።

በክልሉ የታወጀውን የሀዘን ቀናት አስመልክተው ትላንት ጥቅምት 2 ቀን 2016 ዓ.ም የክልሉ ግዜያዊ ፕሬዝዳንትን አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ የተለያዩ ከፍተኛ ሀላፊዎች ጋዜጣዊ መግለጫ መስጠታቸውን የተመለከቱ ዘገባዎች በመገናኛ ብዙሃኑ ተሰራጭቷል።

የሀዘን ቀናቱን አስመልክተው የክልሉ ግዜያዊ ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በሰጡት መግለጫ ለሁሉም የትግራይ ህዝብ መጽናናቱን ይስጥህ፣ መጽናናቱን ይስጠን ማለት እፈልጋለሁ ብለዋል። የልጆቻችን እና ወንድሞቻችን መስዋዕትነት የሁላችንም መስዋዕትነት ነው፣ ለትግራይ ህልውና የተከፈለ ዋጋ ነው እና ለዚህ የሚመጥን ክብር ሰጥተን እርስ በራሳችን የምንጽናናበት ብቻ ሳይሆን ሊያስፈጽሙት የከፈሉለትን የህይወት ዋጋ ሙሉ ለሙሉ ለማረጋገጥ የሚያስችል ወኔ ሰንቀን ስራ የምንሰራበት ነው የሚሆነው ሲሉ ተናግረዋል።

አሁንም ያልተቋጩ ቀሪ የቤት ስራዎች አሉ ሲሉ የተደመጡት አቶ ጌታቸው ህልውናችንን በተሟላ መልኩ ማረጋገጥ በመስዋዕትነታቸው የተረጋገጠው አንጻራዊ ሰላም  ወደ ተሻለ ደረጃ የሚሸጋገርበት ሁኔታ መፍጠር ይገባናል ብለዋል።

በመቀሌ የሰማዕታት ሀውልት ዛሬ ጠዋት ሰማዕታቱን የመዘከር ስነስርአት የተከበረ ሲሆን የክልሉ ባንዲራም ዝቅ ብሎ እንዲውለበለብ ተደርጓል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button