ፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በአማራ ክልል በሶስት ዙር በተደረገው ዘመቻ በሃያ ቀናት ውስጥ አብዛኞቹ የክልሉ ዞኖች ወደ መደበኛ ሁኔታ መመለሳቸውን የአስቸኳይ ጊዜ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ አስታወቀ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 18/2015 ዓ.ም፡- የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ነሐሴ 17 ቀን 2015 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ በአማራ ክልል በሶስት ዙር በተደረገው ዘመቻ በሃያ ቀናት ውስጥ አብዛኞቹ የክልሉ ዞኖች ወደ መደበኛ ሁኔታ መመለሳቸውን አስታውቋል።

በአማራ ክልል ባሕር ዳርን ጨምሮ የዞንና የወረዳ ከተሞችን በመቆጣጣር፣ እሥረኞችን በማስለቀቅ፣ ለዝርፊያ እንዲመቸዉ ቁልፍ መሠረተ ልማቶችን በማውደምና በአማራ ክልል ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓቱን በነፍጥ እና በመንጋ በመናድ እኩይ ፖለቲካዊ ፍላጎቱን ለማሳካት ያለመዉ ጽንፈኛና ዘራፊ ኃይል ፍላጎትና ድርጊት ማክሸፉን ዕዙ በግምገማዉ ማረጋገጡን በመግለጫው አመላክቷል።

በዚህም የአማራ ክልልንም ከዝርፊያ፣ ወድመትና የመፍረስ አደጋ መታደግ መቻሉን ገልጿል። በመሆኑም የክልሉን ዞኖች ከባሕር ዳር ከተማ ጋር የሚያገናኙትን ጨምሮ ክልሉን ከአዲስ አበባ ጋር የሚያገናኙና ተዘግተዉ የነበሩ ዋና ዋና መንገዶችና አብዛኞቹ መሥመሮች ለትራስፖርትና ለመደበኛ እንቅስቃሴ ክፍት እንዲሆኑ  ተደርገዋል ብሏል።

በተጨማሪም የአስቸኳይ ጊዜ ዐዋጅ ጠቅላይ መምሪያ ዕዝ ባወጣው መግለጫ  ሁሉም የመንግሥትና የግል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የተሟላ መደበኛ አገልግሎት መስጠት መጀመራቸውን አስታውቆ ሕዝቡ ለመከላከያ ሠራዊት እያሳየ ያለው አቀባበል፣ የስንቅና የማበረታቻ ድጋፍ በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መሆኑን አረጋግጫለሁ ብሏል።

በተለያዩ አካባቢዎች በኪስ ቦታዎች እየተሰበሰቡና በቡድን እየተደራጁ መንገድና ሱቆችን ለመዘጋት፣ ዝርፊያና በመሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት ለመፈጸም፣ የተዛቡና የተሳሳቱ መረጃዎችን በማሰራጨት ህብረተሰቡን ለመደናገር ቢሞክሩም አልተሳካላቸውም ብሏል።

የተጀመረዉን ሰላምና መረጋገት ይበልጥ ለማጽናትና አስተማማኝ ለማድረግ ወታደራዊ ኦፕሬሽኑ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ዕዙ ጥብቅ መመሪያ መስጠቱን ጠቁሟል።

ከዘራፊና ጽንፈኛ ኃይሎች በጸዱ አካባቢዎች የድርጊቱ ዋና ዋና ተዋናዮች በሕግ ቁጥጥር ሥር እንዲዉሉ እየተደረገ መሆኑንም አስታውቋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ከአንዳንድ ኪስ ቦታዎች በቀር ሰላማዊ ሁኔታዉና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የፈጠረለትን አጋጣሚ በመጠቀም አርሶ አደሩ ወደ መኸር አዝመራ ሥራው መመለሱንና የግብርና ግብአቶች ወደየ አካባቢዎቹ እየተጓጓዙ መሆኑን ገልጿል።

ዕዙ ክልሉ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴ እንዲመለስ ላደረጉ የጸጥታ አካላት፣ ለሕዝቡና በየደረጃዉ ላሉ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የቀጠናና በስራቸዉ ላሉ የኮማንድ ፖስት መምሪያ አባላት ምስጋናውን አቅርቧል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button