ዜናፖለቲካ

ዜና፡ በአዲስ አበባ ሰልፍ ጠርተው የነበሩት ፖለቲከኞች፤ በመጪው እሁድ በመቀለ ሰልፍ እንደሚያደርጉ አሳወቁ

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 17/ 2016 ዓ/ም፡ ከሦስት ሳምንት ገደማ በፊት በአዲስ አበባ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ጠርተው የነበሩት ፖለቲከኞች፤ በመጪው እሁድ በትግራይ መዲና መቀለ ከተማ ከ100 ሺህ በላይ ነዋሪዎች የሚሳተፉበት ተመሳሳይ ሰልፍ እንዳርጋለን ሲሉ ገለጹ።

አስተባባሪዎቹ በመቀለ ከተማ የሚገኘው ንዑስ ኮሚቴም ታህሳስ 5/2016 ዓ.ም. ሰልፉን እንደሚያደርጉ ለመቀለ ከተማ አስተዳደር ማስታወቁን ሲገልጹ የከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ “በከተማዋ የሚደረግ ሰልፍ የለም” ሲል መግለጹን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

በመጪው እሁድ ታህሳስ 21፤ 2026 ዓ.ም. በትግራይ ክልል መዲና መቀለ ከተማ ሊደረግ የታቀደውን ሰላማዊ ሰልፍ እያስተባበሩት ያሉት በአዲስ አበባ ከተማ ኅዳር 30/2016 ዓ.ም. ሊደረግ ታቅዶ የነበረው ሰልፍ የጠሩት ከአስር በላይ ፖለቲከኞች ናቸው።

ሰላማዊ ሰልፍ በመቀለ ከተማ ለማካሄድ “ከማዕከሉ [ኮሚቴ] ጋር የሚናበብ ቡድን” በትግራይ ክልል ማቋቋሙን የኮሚቴው አባል የሆኑት የኢሕአፓ ሊቀመንበር ረዳት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

በመቀለ ከተማ የሚገኘው ንዑስ ኮሚቴም ታህሳስ 5/2016 ዓ.ም. በከተማዋ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚያደርግ ለመቀለ ከተማ ካንቲባ ጽህፈት ቤት በደብዳቤ ማስታወቁንም አቶ ይስሃቅ ገልጸዋል። የአስተባባሪዎቹ ደብዳቤ “በመላው ኢትዮጵያ በማንነታቸው ምክንያት የታሰሩ የትግራይ እና የሌሎች ብሔር ተወላጆች ይፈቱ፣ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደ ቀዬያቸው ይመለሱ” የሚሉ ጥያቄዎችን ለማሰማት መሆኑን ተጠቅሷል። 

በሰልፉ ላይ ይነሳል የተባለው ሌላኛው ጥያቄ ጦርነት እንዲቆም የሚጠይቅ ነው። “ሁሉም ሀገራዊ እና ክልላዊ የፖለቲካ ልዩነቶች እና ችግሮች በፖለቲካዊ ዉይይት ይፈቱ” የሚል ሀሳብም ተቀምጧል።

የመቀለ ከተማ የኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ከሁለት ቀናት በፊት በገጹ በለጠፈው ደብዳቤ “በመቀለ ከተማ የሚካሄድ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሌለ እያመለከትን፤ በዚህ መሠረት የጸጥታ አካላት ጥብቅ ክትትል እንዲያደርጉ እናስታውቃለን” ሲል ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩ እውቅና እንደሌለው ገልጿል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የሰልፉ አስተባባሪዎች አቶ ይስሃቅ እና አቶ አማኑኤል ይህንን ደብዳቤውን መመልከታቸው ገልጸው  “ደብዳቤው የተጻፈው በክልሉ ለሚንቀሳቀሱ የመገናኛ ብዙሃን ተቋማት ነው፤ ለእኛ የደረሰን ደብዳቤ የለም” ብለዋል።

ከሰፈሩት አስተባባሪዎች አንዱ የሆኑት አቶ አማኑኤል ሐዱሽ፤ “ከተማ ከንቲባ ጽህፈት ቤት አዎንታዊ ምላሽ ነው የተሰጠን። ያንን አዎንታዊ ምላሽ ይዘን የራሳችንን አንዳንድ ዝግጅቶች እያደረግን እንገኛለም” ሲሉ ገልጸዋል።

ሌላኛው የሰልፉ አስተባባሪ አቶ ይስሃቅ ወልዳይ፤ “ምላሽ የተሰጠው እኛ ያስገባነው ደብዳቤ [ግርጌ] ላይ ነው። ፊርማ እና ጽሁፉ ደብዳቤው ላይ ነው የተሰጠው” ሲሉ ከከተማዋ ከንቲባ ጽህፈት ቤት ምላሽ የተሰጠበትን መንገድ አስረድተዋል።

ከመቀለ ውጪም ሰባት በሚሆኑ ሌሎች ከተሞችም ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ለቢቢሲ የሚናገሩት ሌላኛው የሰልፉ አስተባባሪ አቶ ይስሃቅ ወልዳይ፤ የመቀለ ከተማው ዝግጅት ቀድሞ መጠናቀቁን አስረድተዋል።

የሰልፉ አስተባባሪዎች ኅዳር 30 ቀን 2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ለማካሄድ የነበረው ሰልፍ “በመንግስት ጫና” ምክንያት ላልታወቀ ግዜ ተራዝሟል ሲሉ ማሳወቀቸው ይታወቃል። ሰልፉ ለሌላ ጊዜ የተላለፈው መንግስት የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላትን በማሰሩ እና አሉታዊ የተባሉ እርምጃዎች በመውሰዱ መሆኑን ኮሚቴው ህዳር 29 በአዲስ አበባ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ አስታውቋል። አራት የሰልፉ አስተባባሪ ኮሚቴ አባላት መታሰራቸውንም ገልጿል።

ኮሚቴው “መንግስት ሰላማዊ ሰልፉን የተለያዩ ፀረ-ሰላም ሃይሎች ያዘጋጁት እንደሆነ በማስመሰል የሰልፉ ቀን የጸጥታ ሃይሎችን የማሰማራት ፍላጎት የሌለው መሆኑን በመግለጽ ሰላማዊ ሰልፉን አቅጣጫ በማሳት አደናቅፏል” ሲል መንግስትን ከሷል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button