ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና፡ በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የሚከሰቱ ግጭቶችን በዘላቂነት ለመፍታት መስማማታቸውን አስታወቁ

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 11/ 2016 ዓ/ም፦ በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢዎች የተከሰቱ ግጭቶችን በውይይት በዘላቂነት ለመፍታት ከስምምነት መደረሱን የየክልሎቹ ርዕሳነ መስተዳድሮች ገለጹ።

የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባ እና የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ መሀመድ ስምምነቱን በተመለከተ ዛሬ ሐምሌ 11 ቀን በጋራ  መግለጫ ሰጥተዋል። 

የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ “አልፎ አልፎ እየተነሳ ያለውን ችግር ከስር መሰረቱ ለመፍታትና ተመልሶ እንዳይነሱና የሰው ሕይወት መጥፋት ስለሌለበት ስምምነት መደረጉን” አረጋግጠዋል።

የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው እንዲመለሱ ስምምነት ላይ በመደረሱ ዘለቂ ሰላም በአዋሳኝ አካባቢዎች እንዲኖር ክልሉ በቁርጠኝነት ይሰራል ማለታቸውን አዲስ ዋልታ ዘግቧል።

የግጭቱ መነሻ የሆኑ ጥያቄዎች በህጋዊ፣ ህገ መንግስታዊ  እና ሰላማዊ በሆነ አግባብ ብቻ እንዲመለሱ በፌዴራል ባለድርሻ አካላት የሚመራ መሆኑን ገልፀው ሰላም እንዲመጣ እንሰራለን ብለዋል።

በሰኔ ወር በሁለቱ ክልሎች አዋሳኝ አካባቢ በተቀሰቀሰ ግጭት በርካታ ሰዎች መሞታቸውን እንዲሁም መፈናቀላቸውን አዲስ ስታንዳርድ መዘገቡ ይታወሳል።  በተጨማሪም በርካታ ሰዎች መታገታቸውንና መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በተመሳሳይ ወር ባወጣው መግለጫ በአፋር እና ሶማሌ ክልሎች ወሰን አከባቢ የተቀሰቀሰው ግጭት ሊቆምና ዘላቂ ሰላም የሚያሰፍን መፍትሔ ሊበጅለት እንደሚገባ አሳስቧል። 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በአፋር እና በሶማሌ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች ረጅም ጊዜ ያስቆጠረውን አለመግባባት ለመፍታት በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚደንት የሚመራ 25 አባላት ያሉት የዕርቀ ሰላም ኮሚቴ መቋቋሙ ይታወሳልአስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button