ዜናማህበራዊ ጉዳይ

ዜና፡ በኢትዮጵያ ተጠልለው የሚገኙ 916 ሺ ስደተኞችን የዲጂታል ስርአቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ስምምነት ላይ ተደረሰ

አዲስ አበባ፣ ጥር 18/2016 ዓ.ም፡- በኢትዮጵያ የተጠለሉ ስደተኞችን የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሚያደርግ የመግባቢያ ስምምነት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና በዓለም አቀፉ የስራ ድርጅት መካከል ተፈረመ።

በዚህም በኢትዮጵያ ተጠልለው የሚገኙ 916 ሺ ስደተኞችን የዲጂታል ስርአቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ስምምነቱ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንዳለው ተጠቁሟል።

ስምምነቱ በዲጂታል ክህሎት አካታች ስትራቴጂ ጥናት፣ በዲጂታል ዘርፍ የቴክኒክ ስልጠና እና በዲጂታል ኢኖቬሽን ሀብት ግንባታ ዙሪያ በጋራ ለመስራት ያስችላል መባሉን የጠቆመው የኢዜአ ዘገባ ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶክተር በለጠ ሞላና በዓለም አቀፉ የስራ ድርጅት የኢትዮጵያ የጅቡቲ፣የሶማሊያ፣የሱዳንና የደቡብ ሱዳን ቀጠና ዳይሬክተር አሌክሶ ሙሲንዶ መፈረማቸውን አስታውቋል።

የመግባቢያ ስምምነቱ ስደተኞችንና በአካባቢው የሚኖረውን ማህበረሰብ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ምቹ የስልጠና እና የስራ እድል ተጠቃሚ ለማድረግ የሚያስችል ነው መባሉን ዘገባው ጠቁሟል።

በኢትዮጵያ እኤአ በ2025 አሳታፊ ዲጂታል መር የኢኮኖሚ ልማት ለመገንባት እየተሰራ መሆኑን በመጠቆም ለዚሁ ስኬት የሚረዳ ስራቴጂ ተቀርጾ ወደ ስራ መገባቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ተናግረዋል ያለው ዘገባው ስምምነቱ የዲጅታል መሰረተ ልማትን ለማሟላትና በሀገሪቱ ተጠልለው የሚገኙ ስደተኞች በዘርፉ ያላቸውን ክህሎት እንዲያሳድጉ የሚረዳ ነው ማለታቸውንም አካቷል።

የቀጠናው አገራት የአለም ሰራተኞች ድርጅት ተወካይ አሌክሶ ሙሲንዶ በበኩላቸው፤ ድርጅታቸው አካታች የዲጅታል ኢኮኖሚ ለመገንባት ለሚደረገው ጥረት ድጋፍ እንደሚያደርግ በመግለጽ በኢትዮጵያ የሚገኙ በርካታ ስደተኞች የዲጅታል ክህሎትን በማሳደግ የሚያጋጥማቸውን የመረጃ ክፍተት ለመሙላትና የስራ ዕድል ተጠቃሚ እንዲሆኑ ለማስቻል ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር በቅርበት ለመስራት መስማማታቸውን ጠቁመዋል።

በተጨማሪም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ፓርክ ኮርፖሬሽን እና የሶማሌ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ከአለም አቀፍ የስራ ድርጅት (ILO) ጋር በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ መፈራረማቸውንም ዘገባው አመላክቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ለስምምነቱ ተግባራዊነት የኔዘርላንድ መንግስትና ሌሎች አለም አቀፍ ድርጅቶች ድጋፍ ማድረጋቸው በፊርማ ስነ ስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡ አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button