ማህበራዊ ጉዳይዜና

ዜና፡ በኦሮምያ ክልል የመማሪያ መጽሐፍትን ለእያንዳንዱ ተማሪ ለማዳረስ ሁለት ዓመት ይፈጃል ተባለ

አዲስ አበባ፣ ጥር 16/2016 ዓ.ም፡- በኦሮሚያ ክልል የመማሪያ መጽሐፍትን ለእያንዳንዱ ተማሪ ለማዳረስ ሁለት ዓመት ሊፈጅ እንደሚችል የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ አስታወቀ።

እስካሁን 20 ሚሊዮን የመማሪያ መጽሐፍት ለተማሪዎች የተሰራጨ ቢሆንም የመማሪያ መጽሐፍትን ለሁሉም ተማሪዎች ማዳረስ አለመቻሉ በትምህርታቸው ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እያሳደረ ይገኛል ሲሉ የክልሉ ኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ቶላ በሪሶ (ዶ/ር) መግለጻቸውን የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ዘግባል።

በክልሉ የመማሪያ መጽሐፍትን ለእያንዳንዱ ተማሪ ለማዳረስ ሁለት ዓመት ሊፈጅ ይችላል ማለታቸውንም ጠቁሟል።

በኦሮሚያ ክልል በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አምስት ሚሊዮን፣ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች አንድ ሚሊዮን 54 ሺህ፣ በቅድመ መደበኛ ትምህርት ቤቶች ደግሞ አንድ ነጥብ አምስት ሚሊዮን ተማሪዎች ይገኛሉ ያሉት ኃላፊው፤ በመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለሚገኙ ተማሪዎች መጽሐፍትን የሚያቀርበው የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሲሆን ለሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ደግሞ መጽሐፍትን የማቅረብ ኃላፊነቱ የትምህርት ሚኒስቴር መሆኑን ገልጸዋል።

በዚህም ትምህርት ሚኒስቴር በክልሉ ከዘጠነኛ እስከ 12ኛ ክፍል ድረስ ላሉ ተማሪዎች 14 ሚሊዮን መጽሐፍትን ማቅረብ የሚኖርበት ቢሆንም እስካሁን ድረስ ለክልሉ ማድረስ የቻለው 5 ሚሊዮን (35 ነጥብ 7 በመቶ) መጽሐፍትን ብቻ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የተቀረውን መጽሐፍትን ደረጃ በደረጃ እያተመ ለማቅረብ ቃል መግባቱን የገለጹት ኃላፊው፤ ሚኒስቴሩ ያቀረበውን መጽሐፍት የክልሉ ትምህርት ቢሮ ለተማሪዎቹ ማሰራጨቱን ተናግረዋል። ከሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለዘጠነኛ ክፍል ተማሪዎች በተሻለ ሁኔታ መጽሐፍት ማዳረስ ቢቻልም ሌሎቹ ክፍሎች ላይ ግን ከፍተኛ ችግር አለ ብለዋል።

የአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች መጽሐፍትን አትሞ የሚያሰራጨው የክልሉ ትምህርት ቢሮ መሆኑን ገልጸው፤ ለእነዚህ ትምህርት ቤቶች 36 ሚሊዮን መጽሐፍት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ ቢሮው እስካሁን ድረስ አትሞ ማሰራጨት የቻለው 15 ሚሊዮን መጽሐፍትን መሆኑን ጠቅሰዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

በክልሉ መጽሐፍትን ለእያንዳንዱ ተማሪ ለማድረስ ከዚህ በኋላ ሁለት ዓመት እንደሚፈጅ በክልሉ የትምህርት ትራንስፎርሜሽን መተንበዩን የገለጹት ኃላፊው፤ በዚህ ዓመት ግን አንድ መጽሐፍ ለሁለት ተማሪ ለማድረስ እቅድ መያዙን አብራርተዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button