ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ በካይሮ የተካሄደው የሶስትዮሽ ድርድር ያለውጤት መጠናቀቁን ግብጽ አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 23/2015 ዓ.ም፡- ባለፉት ሁለት ቀናት በግብጽ ካይሮ ሲካሄድ የነበረው የህዳሴ ግድብ የሶስትዮሽ ድርድር ያለውጤት መጠናቀቁን የግብጽ የመስኖ እና ውሃ ሀብት ሚኒስቴር አስታወቀ። ድርድሩ ያለውጤት የተጠናቀቀው በኢትዮጵያ አሁንም ያልተቀየረ አቋም ነው ሲል ሚኒስቴሩ በመግለጫው ተችቷል።

ግብጽ በግድቡ አሞላል እና አስተዳደር ዙሪያ በድርድር አስገዳጅ ህጋዊ ስምምነት እንዲደረስ እንደምትፈልግ ያስታወቀው ሚኒስቴሩ ሁሉም ተደራዳሪዎች ለቀጣይ ድርድር ሊያግባባ የሚችል ራእይ ሰንቀው እንዲቀርቡ አሳስቧል።

በተመሳሳይ ትላንት ድርድሩ ከተጠናቀቀ በኋላ ኢትዮጵያን ወክሎ የሚደራደረው ቡድንን የመሩት በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ዶ/ር ኢንጂነር ስለሺ በማህበራዊ ሚዲያ ትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ በኢትዮጵያ፤ ግብጽና ሱዳን መካከል ስናደርግ የነበረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሁለት ቀናት የሶስትዮሽ የመጀመሪያ ሙሌት (ግድቡ በጥቂት አመታት ሙሉ ደረጃ እስኪደርስ) እና ውሃ አለቃቀቅ ድርድር ተጠናቋል ብለዋል፡፡ በበርካታ የስምምነት አንቀጾች ላይ ስምምነት ለመድረስ ውይይቱ በመስከረም ወር በአዲስ አበባ እንደሚቀጥል የጠቆሙት አምባሳደሩ የኢትዮጵያ ወገን ውሃውን በቀጣይ ፍትሃዊና ምክንያታዊ አጠቃቀምን በሚያረጋግጥ መልኩ እና በቀጣናው ትብብር እንዲጎለብት በሚያስችል መንገድ እየሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን በህዳሴ ግድብ ዙሪያ ሲያካሂዱት የነበረው ድርድር ከተቋረጠ ሁለት አመት ከአምስት ወር ሁኖታል፤ ይሁን እንጂ ትላንት ነሃሴ 21 ቀን 2015 ዓ.ም የሶስትዮሽ ድርድሩ በካይሮ እንደገና መጀመሩን ከሁሉም ቀድመው የግብጽ መስኖ ሚኒስትር አብስረዋል። አለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃንም ጉዳዩን ተቀባብለው እያሰራጩት ይገኛሉ። ነሃሴ 22 ቀን 2015 ዓ.ም ዘገባችን በካይሮ እየተካሄደ ያለው የሶስትዮሽ ድርድር በስምምነት ይጠናቀቃል የሚል ተስፋ እንደተጣለበት መጠቆማችን ይታወሳል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button