ዜና፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ የመሾም ሂደት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26/2016 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ የነበሩት ወ/ሮ ብርቱካን ሚዴቅሳ በገዛ ፈቃዳቸው ስራ መልቀቃቸውን ተከትሎ በምትካቸው ያልተሾለት የምርጫ ቦርድ ለቦታው የሚመጥን ሰው የመሾም ሂደት እንተጀመረ ተገለጸ። ለዚህም ተግባር በሚል ጠ/ሚኒስትር ዶክተር አቢይ አህመድ ስምንት አባላት ያሉት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴ መሰየማቸውን ኢዜአ በዘገባው አስታውቋል።

የኢፌዴሪ ህገ መንግሥት አንቀጽ 102 እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ማቋቋሚያ አዋጅ 1133/2011 አንቀፅ 5/1 ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዕጩ የስራ አመራር ቦርድ አባላት የሚመለምል ገለልተኛ ኮሚቴ እንደሚሰይሙ ይደነግጋል ያለው ዘገባው በዚሁ መሰረትም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ስምንት አባላት ያሉት የዕጩ ሰብሳቢ መልማይ ኮሚቴ ከጥቅምት 23/2016 ዓ.ም. ጀምሮ መሰየማቸውን እና አባላቱ የተጣለባቸውን ከባድ ኃላፊነት በቅንነት፣ በትጋትና በታማኝነት እንዲወጡ ማሳሰባቸውን አስታውቋል።

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ዕጩ መልማይ ኮሚቴው ወደ ስራ የገባ ሲሆን በቅርቡም ጥቆማ መቀበል ይጀምራል ተብሏል።

የመልማይ ኮሚቴ አባላቱን በሰብሳቢነት የሚመሩት ቀሲስ ታጋይ ታደለ መሆናቸውን የጠቆመው ዘገባው ፕሮፌሰር ተከተል ዮሐንስ፣ አቶ ባዩህ በዛብህ፣ ዶክተር ዮሐንስ በንቲ፣ አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ ወይዘሮ ርግበ ገብረሃዋርያ፣ ወ/ሮ እንግዳዬ እሸቴ፣ ኢንጂነር መላኩ እዘዘው፣ በአባልነት መሰየማቸውን አስታውቋል። አስ

Exit mobile version