ማህበራዊ ጉዳይዜናፖለቲካ

ዜና፡ “የመግባቢያ ስምምነቱ መልካም ጉርብትናን የሚፈጥር እና የጎረቤት ሀገር መብት የሚጠብቅ ነው” ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደርና የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ገለጹ

አዲስ አበባ፣ ጥር 4/ 2016 ዓ/ም፦ በኢትዮጵያና በሶማሌላንድ መካከል ሁሉን አቀፍ የትብብርና የአጋርነት መግባቢያ ስምምነት ሰነድ መፈራረም መልካም ጉርብትናን በመፍጠር ዘላቂ የልማት ትስስርን የሚያጠናክር ነው ሲሉ የሶማሌ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ገለጹ። 

የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ “የጋራ መግባቢያ ስምምነቱ ብሔራዊ ጥቅማችንን በሚያሳካ መልኩ የጎረቤቶቻችንን መብት በማይነካ መልኩ የተደረገ ስምምነት ነው” ሲሉ ገልጸዋል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሙስጠፌ ሙሃመድ በኢትዮጵያና ሶማሌላንድ በቅርቡ የተፈረመውን ስምምነት አስመልክቶ ትላንት በጽህፈት ቤታቸው መግለጫ ስጥተዋል። ርዕሰ መስተዳድሩ በመግለጫቸው፤ “ስምምነቱ ሀገራችን የባሕር በር እንድታገኝ ከማድረጉም ባለፈ ከሶማሌላንድ ጋር ያለንን መልካም ጉርብትና እንደሚያጠናክር” ተናግረዋል። 

ስምምነቱ በተለይ ክልሉ ካለው የእንስሳት ሃብት የተሻለ ጥቅም እንዲያገኝም የሚያስችል ነው ብለዋል። በዚህም የክልሉ አርብቶ አደር ለእንስሳቱ ገበያ የተሻለ አማራጭን እንደሚያስገኝለትም አቶ ሙስጠፌ በመግለጫቸው ጠቁመዋል።

ርዕሰ መስተዳድሩ ”ኢትዮጵያ በሰጥቶ መቀበል መርህ የወታደራዊ ቤዝና ኮሜርሻል ማሪታይም አገልግሎት ለማግኘት የደረሰችው ስምምነት መልካም ጉርብትናን በማምጣት ሌላውን ሳንጎዳ የሀገራችንን ስብራት የሚጠግን ነው” ብለዋል።

“የጋራ መግባቢያ ስምምነቱ ብሔራዊ ጥቅማችንን በሚያሳካ መልኩ የጎረቤቶቻችንን መብት በማይነካ መልኩ የተደረገ ስምምነት ነው” ሲሉ የገለጹት የክልሉ ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ኢንጂነር መሀመድ ሻሌ ገለጸዋል

የሶማሌላንድ ህዝብና የሶማሌ ክልል ህዝቦች የጋራ የሚያደርጋቸው በርካታ ጉዳዮች መኖራቸውን ገልጸው የጋራ መግባቢያ ስምምነቱ ብሔራዊ ጥቅምን በሚያሳካ መልኩ የጎረቤቶቻችንን መብት በማይነካ መልኩ የተደረገና በጋራ ተጠቃሚነት መርህ መሰረት የተከናወነ ነው ብለዋል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የስምምነቱ የመጀመሪያ ተጠቃሚ ክልል ነዋሪዎች መሆናቸውን ጠቁመው ህዝቡን በወደቡ ዙሪያ የሚታዩ ብዥታዎችን ለማጥራት የፓርቲው አባላትና አመራሮች ቀጣይነት ያለው ስራ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button