ዜና፡ የአፍሪካ ህብረት የሰላም ስምምነቱ ተቆጣጣሪ ኮሚቴ የቆየታ ጊዜው እንዲራዘም የውሳኔ ሃሳብ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24/ 2016 ዓ/ም፦ የአፍሪካ ህብረት የክትትል፣ ማረጋገጥ እና የተልዕኮ የማስከበር አላማ ሰንቆ የሚንቀሳቀሰው ኬሚቴ የቆይታ ጊዜው በአንድ አመት እንዲራዘም ለኅብረቱ ኮሚሽን የውሳኔ ሃሳብ አቀረበ።

ኮሚቴው ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታት፣ መበተን እና መልሶ ማቋቋም ሂደት (DDR) እና ተፈናቃዮችን መልሶ ማቋቋም ተልዕኮው ከታህሳስ 22፣ 2016 ወደ ታህሳስ 22/ 2017 እንዲራዘም የጠየቀው በህብረቱ 3ኛው የጋራ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነው።

በስበሰባው ከፌዴራል መንግስት፣ ከህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እና ከአፍሪካ ህብረት ከፍተኛ አመራሮች የተውጣጡ ተወካዮች የተሳተፉ ሲሆን፣ ተወካዮቹ ህዳር 2022 የተደረሰውን ዘላቂ ጦርነት የማቆም ስምምነተ አተገባበር ሂደት፣ ፈተናዎች እና አስጊ ጉዳዮች ላይ ግምገማ አድርጓል። 

ተልዕኮውን ማራዘሙ የተፈለገው ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታት፣ መበተን እና መልሶ ማቋቋም ሂደትን ማፋጠን እና የተፈናቀሉ ዜጎችን መልሶ የማቋቋሙ ስራን ቅድሚያ መስጠት ላይ በማቶከር በኢትዮጵያ ያለውን የሰላም ሂደቱን ወሳኝ ጉዳዮችን ለመፍታት በማለም መሆኑን የአፍሪካ ህብረት ባወጣው መግለጫ ገልጿል።

ሂደቱን ለማጠናከርም የአፍሪካ ህብረት በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ ስብሰባ ለማካሄድ አቅዷል። ስብሰባው በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላምና መረጋጋትን ለማስቀጠል የተቀናጀ ጥረት አስፈላጊ መሆኑን በመገንዘብ ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታት፣ መበተን እና መልሶ ማቋቋም ሂደት (DDR) እና ተፈናቃዮችን መልሶ ማቋቋም እና በአጠቃላይ የሰላም ተነሳሽነት ላይ የበለጠ ስትራቴጂ ለመንደፍ ያለመ ነው።

የአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን በሰምምነቱ መሰረት ተዋጊዎችን ትጥቅ ማስፈታት፣ መበተን እና መልሶ ለማቋቋም የሚውል አድን ሚልዮን ዶላር መመደቡን በመግለጫው ገልጿል፡፡

በተጨማሪም የአፍሪካ ኅብረት ከኢትዮጵያ መንግሥትና ህዝቦቹ ጎን በመቆም ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን ያለውን ቁርጠኝነት በአጽንኦት አስታወቋል።አስ

Exit mobile version