ዜናቢዝነስ

ዜና፡ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሮልስ ሮይስ ኩባንያ ጋር የኤርባስ አውሮፕላኖቹን የሞተር ደህንነት ለማስጠበቅ የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራረመ

አዲስ አበባ፣ ህዳር 7/2016 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሚጠቀምባቸውን ኤርባስ አውሮፕላኖቹን የሞተር ደህንነት እንዲያስጠብቅለት ከሎርስ ሮይስ ጋር ስምምነት መፈጸሙ ገለጸ።

የአውሮፕላን ሞተር በማምረት የሚታወቀው ሮልስ ሮይስ ሙሉ ጥገና እና ከበራራ በፊት አውሮፕላኖቹ ዝግጁ መሆናቸውን ለማረጋገጥ የሚደረግ ሁሉን አቀፍ ፍተሻ የማድረግ አገልግሎት እንደሚሰጥ በስምምነቱ መካተቱንም አየር መንገዱ አስታውቋል።

ሮልስ ሮይስ አገልግሎቱን የሚሰጠው የአየር መንገዱ ንብረት ለሆኑት እና ትሬንት ኤክስደብልዩቢ 84 (Trent XWB-84) ተብሎ የሚጠራ ሞተር ለተገጠመላቸው ኤርባስ አውሮፕላኖች መሆኑን ጠቁሟል። ሮልስ ሮይስ የሚሰጠው አገልግሎት የረቀቀ እና ደረጃው ከፍ ያለ የቁጥጥር ስርአትን በመጠቀም መሆኑንም አመላክቷል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ2016 የኤርባስ አውሮፕላኖችን መጠቀም ከጀመረ ወዲህ የሮልስ ሮይስ ኩባንያ ወነኛ ደንበኛ መሆኑም ተገልጿል። ሮልስ ሮይስ ለአየር መንገዱ የኤርባስ ሞተሮችን ከማደስ በተጨማሪ ለሌሎቹ አውሮፕላኖቹ በተለይም ለቦይንግ 787 አውሮፕላኖቹ የሞተር ሽያጭ እንደሚፈጽም ተገልጿል።

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button