ዜና

ዜና፡ የኦፓል ማዕድን ዋሻ የተናደባቸውን ማዕድን አውጭዎችን ለማትረፍ ዘመናዊ ማሽኖች ድጋፍ እንዲደረግ ተጠየቀ 

አዲስ አበባ፣ ያካቲት 6/2016 ዓ/ም፦ በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደላንታ ወረዳ 018 ቀበሌ ላለፉት 13 አመታት የኦፓል ማዕድን ቁፋሮ ሲደረግበት የቆየው ዋሻ ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት 6፡30 አካባቢ ተንዶ በዋሻው ውስጥ የቀሩ ሰዎችን የማውጣት ስራ ስድስተኛ ቀኑን ይዟል። 

የደላንታ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አያለው በሪሁን ለአዲስ ስታንዳርድ እንዳስታወቁት በማዕድን ቁፋሮ ላይ የነበሩ በግምት ዘጠኝ የሚሆኑ የማዕድን አውጭዎች ላይ ዋሻው መናዱን እና ሰዎቹን ለማትርፍ የሚደረገው ጥረት ከወረዳው አቅም በላይ መሆኑን ገልጸዋል። 

ማዕድን አውጪዎቹን ለማትረፍ 50 የሚሆኑ ሰዎች ቁፋሮ እያከናወኑ መሆኑን እና እስከዛሬ 80 ሜትር ቁፋሮ መደረጉን ተናግረዋል። ቦታው ቆላማ እና መልክአ ምድሩ አስቸጋሪ በመሆኑ ችግሩን ባጭር ጊዜ እንዳይፈታ አድርጓል ብለዋል።

“በዚህም ምክንያት ሰዎቹን የማትረፍ ስራው ከአቅማችን በላይ ሆኗል” ሲሉ አስተዳዳሪው ለአዲስ ስታንዳርድ ገልጸዋል።  በመሆኑም ሰዎቹን ከተደረመሰው የማዕድን ዋሻ ውስጥ ለማውጣት የሚረዳ ዘመናዊ ማሽኖች ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል። 

ዋሻው ላለፉት 13 አመታት ኦፓል ለማውጣት ቁፋሮ ሲከናወንበት የቆየ በመሆኑ በውስጡ የነበሩ መሶሶውች የላኛውን መሬት ክብደት መሸከም ባለመቻላቸው ተደርምሷል ብለዋል።

ከዚህ በፊት 2005 ዓ/ም ተመሳሳይ አደጋ መከሰቱን እና ከ11 ቀናት በኋላ በህይወት የተገኘ ሰው መኖሩን አስታውስዋል። ይህን ተስፋ በማድረግ በአሁኑ አደጋ ስድስተኛ ቀናቸውን ያያዙት ሰዎችም በህይወት ለማትረፍ እየሰራን ነው ብለዋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button