ዜናፖለቲካ
በመታየት ላይ ያለ

ዜና፡ የፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዳይተገበር የትግራይ ግዜያዊ አስተዳደር እያጓተተ ነው ሲል የፌደራል መንግስቱ ወቀሳ አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 26/2016 ዓ.ም፡- የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነትን አንደኛ አመት አስመልክቶ የፌደራል መንግስቱ ባወጣው መግለጫ በፕሪቶርያውን ስምምነት አተገባበር ላይ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በአንዳንድ ነገሮች ወደኋላ እየቀረና ስምምነቱን በተሟላ ሁኔታ ሳይፈጽም እያነከሰ ነው ሲል ወቀሳ ሰንዝሯል። ለስምምነቱ ትግበራ የፌደራል መንግስቱ ከሚጠበቅበት በላይ ተጉዟል ሲል ገልጿል።

የፕሪቶርያ ስምምነት ሙሉ በሙሉ እንዲከበር መንግሥት አሁንም ቁርጠኛ አቋም አለው ያለው መግለጫው ሁሉም አካላት ተመሳሳይ ቁርጠኝት በማሳየት የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት ሊወጡ ይገባል ሲል አሳስቧል፡፡

የፌደራል መንግስት በኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት በኩል የፕሪቶርያ የሰላም ስምምነትን አንደኛ አመት አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በተመሠረተ ጊዜ የአመራሩን ድርሻ ክልሉ እዲወስድ ማድረጉን፣ የግብርና ሥራውን ለማገዝ በግብርና ሚኒስቴር በኩል ከሚጠበቅበት በላይ መስራቱን፣ ዩኒቨርሲቲዎችንና ትምህርት ቤቶችን ወደ አገልግሎት ለመመለስ የትምህርት ሚኒስቴር ከተልዕኮ በላይ መጓዙን፣ የመከላከያ ሠራዊት የሕዝቡን ችግር ለመፍታት ከራሱ በጀት ቀንሶ አያሌ ተግባራት ማከናወኑን በዝርዝር አስቀምጧል።

አንዳንድ ነገሮችን እያገዘ፤ አንዳንድ ነገሮችን ችሎ እያለፈ፤ አንዳንድ ነገሮችን እየመከረ፤ አንዳንድ ነገሮችንም ራሱ እየሠራ የሰላም ስምምነቱ በተሟላ ልኩ በሂደት እንዲፈጸም ለማድረግ ሞክሯል ብሏል፡፡

አከራካሪ የሚባሉ አካባቢዎችን በተለከተ የፌዴራል መንግሥቱ አቋም ወስዶ ሠርቷል ያለው የኮሙዩኒኬሽን አገልግሎቱ መግለጫ የፌዴራል መንግሥት በዚህ ረገድ ያለው አቋም ዘላቂ ሰላምን የሚያረጋግጥ፣ ሁሉንም ወገን በሚጠቅም መንገድ፣ ኅብረ ብሔራዊ አንድነትና ብልጽግና በሚያረጋግጥ መንገድ ፍትሔ መሰጠት እንዳለበት መሆኑን አመላክቷል።

ክረምት ደርሶ የእርሻ ሥራ ከመጀመሩ በፊት ተፈናቃዮች ወደ አካባቢያቸው እንዲመለሱ፤ የአካባቢ ነዋሪዎች በመረጧቸው አካላት እንዲተዳደሩ፤ በመጨረሻም ደረጃ በደረጃ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ አቅጣጫ ማስቀመጡን ጠቁሟል።

ይሄንንም ተግባራዊ ለማድረግ እንቅስቃሴ እተደረገ ይገኛል ያለው መግለጫው እነዚህን ሁሉ አቋሞችና ተግባራት የኢትዮጵያ ሕዝብና የዓለም አቀፉም ማኅበረሰብ በሚገባ ያውቃል ብሏል፡፡

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ይህ ሁሉ ቢደረግም እንኳን በዚያኛው ወገን እግር የመጎተት አዝማሚያ ይታያል ሲል ወቅሶ፡ ይህ ግን ዘላቂ ሰላምን፣ ብልጽግናንና የሕዝቦችን ኅብረ ብሔራዊ አንድነት አያረጋግጥም፡ የፌዴራል መንግስት የፕሪቶርያውን ስምምነት በተመለከተ ከሚጠበቅበት በላይ ተጉዟል፣ በዚህም ለሰላም ያለውን ጽኑ አቋም ደጋግሞ አሳይቷል ብሏል፡፡

በትግራይ ከሁለት ዓታት በፊት ተፈጠረው ሁኔታ ወደ ጦርነት ከማምራቱ በፊት መንግሥት የሰላም አማራጮችን ሁሉ ሞክሯል ያለው መግለጫው ወደ ጦርነት የተገባው ያደረጋቸው ጥረቶች ሁሉ ባለመሳካታቸው መሆኑን በዝርዝር አስቀምጧል፤ መንግስት ወደ ጦርነቱ የገባው ተገዶ ነው ሲል ገልጿል።

በጦርነቱ መጨረሻ የፌዴራል መንግስት ሁሉን ነገር በኃይል ለመፈጸም የሚያስችል ወታደራዊ ቁና ነበረው ያለው መግለጫው ነገር ግን ጦርነቱ በሰላም ስምምነት ቢቋጭ ሀገርን አትራፊ የሚያደርግ መሆኑ ስለታመነበት ፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት እንዲፈረም ማድረጉን አስታውቋል።

በጦርነት ሁኔታ ውስጥ ሆኖ ዕርዳታ ለትግራይ ሕዝብ እንዲደርስ መንዶችን ከፍቶ አሳልፏል ያለው መግለጫው የእርዳታ መኪኖች በሄዱበት እየቀሩ እንኳን ከሕዝብ የሚበልጥ የለም በሚል ችግሩን ተቋቁሞ እርዳታ እንዳይቋረጥ አድርጓል ሲል ገልጿል፡፡ አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button