ዜና

ዜና፡ ደቡብ ሱዳን እና ግብጽ የወታደራዊ ትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ጥር 7፣ 2016 ዓ/ም፡ ደቡብ ሱዳን እና ግብጽ ወታደራዊ ትብብራቸውን ለማጠናከር የመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ተፈራረሙ። 

ሁለቱ ሀገራት የምግባቢያ ሰነዱን የተፈራረሙት የደቡብ ሱዳን መከላከያ ሚኒስትር እና ፌዴራል ጉዳዮች ሚንስትር ቾል ቶን ባሎክ በግብጽ ያደረጉትን ጉብኝት ተከትሎ ነው። 

ዓርብ ዕለት በተካሄደው የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ ሚካኤል ማኩዪ ሉት ባደረጉት ንግግር ደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት የተጣለውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ላይ ስጋት እንዳላት ጠቅሰዋል።

የወታደራዊ የትብብር ስምምነቱ በቅርቡ ተግባራዊ ይሆናል ብለዋል። “የመግባቢያ ሰነዱን የግብጽ መከላከያ ሚኒስትር ወደ ደቡብ ሱዳን በማምራት ተግባራዊ መደረግ ይጀመራል” ብለዋል።

ደቡብ ሱዳን የተባበሩት መንግስታት የፀጥታው ምክር ቤት በሀገሪቱ ላይ በጣለው የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ምክንያት መሳሪያ ለመግዛት ምንም አይነት ጥያቄም ሆነ ማመልከቻ ባይቀርብም፤ ሚኒስትሩ ደቡብ ሱዳን ከግብጸ ጋር በወታደራዊ ትብብር ለመስራት ከስምምነት ላይ መድርሷ በእጅጉ ተጠቃሚ እንደሚያደርጋት አስምረውበታል።

ግብጽ ከህዳሴ ግድብ ድርድር በፍቃዷመውጣቷን ተከትሎ በአፍሪካ ቀንድ የዲፕሎማሲያዊ ሰራዎችን እየሰራች ትገኛለች። በቅርቡ የግብጽ ከፍተኛ ላኡክ ቡድን ወደ ሶማሊያ በማምራት ከሃሰን ሼክ ሞሃመድ ጋር ውይይት አደርገዋል። ቡድኑ ኢትዮጵያ እና ሶማሊ ላንድ ያደረጉትን ስምምነት ተከትሎ በሞቃዲሾ ባደረጉት ውይይት ግብጽ ለሶማሊያ ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ያላትን ድጋፍ አርጋግጠዋል። 

ባሳለፍነው ሳምንት ሃሙስ ደግሞ የግብጽ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳመህ ሹክሪ፣ ከፕሬዝዳንት አብድል ፈታ አል ሲሲ የተላከ ድብዳቤ ለኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ በአካል በመሄድ አድርሰዋል። የሚንስትሩ ቀዳሚ ጉብኝት በሁለቱ አገራት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር እና በቀጠናው ልማት በጋራ ጥቀም ላይ ውይይት ለማድርግ ያለም መሆኑ ተገልጿል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button