ዜናፖለቲካ

ዜና፡ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከደቡብ አፍሪካ እና ከታንዛኒያ ኢታማዦር ሹም ጀኔራሎች ጋር በአዲስ አበባ ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 13/ 2016 ዓ ም፦ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የደቡብ አፍሪካ መከላከያ ሰራዊት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀነራል ሩድዛኒን ማፕዋንያንና የታንዛኒያን ኢታማዦር ሹም ጀኔራል ጃኮፕ ጆንን በተናጠል በቢሮቸው ተቀብለው አነጋገሩ።

ጥቅምት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በልዩ ልዩ ክንውኖች ተከብሮ የሚውለው 116ኛው የሠራዊት ቀን በክብር ለመታደም አዲስ አበባ የገቡት ጀነራል ሩድዛኒን ማፕዋንያን በኢትዮጵያ እና በደቡብ አፍሪካ ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት እና ትብብር ለማጠናከር ከፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር ተነጋግረዋል ሲል የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት አስታውቋል። 

በተጨማሪም የሠራዊት ቀንን ለመታደም እና በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት ለማጠናከር አዲስ አበባ መግባታቸው የተነገረው የታንዛኒያ ኢታማዦር ሹም ጀኔራል ጃኮፕ ጆን ከጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ጋር ተወያይተዋል ተብሏል

ሁለቱ ኢታማዦር ሹሞች በሁለቱ ሀገራት ያለውን ወታደራዊ ግንኙነት ለማጠናከር እና በስልጠና ጉዳዮች በጋራ ለመስራት በሚችሉባቸው ሁኔታዎች ዙሪያ መክረዋል፡፡

ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት የሁልቱ አገራት ኢታማዦር ሹሞች በተጨማሪ የተለያዩ የአፍሪካ ሀገራት ኢታማዦር ሹሞችና ወታደራዊ አመራሮች በ116ኛው የሠራዊት ቀን በዓል ላይ ታዳሚ እንደሚሆኑ የመከላከያ ውጭ ግንኙነት እና ወታደራዊ ትብብር ዋና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል ተሾመ ገመቹ አስታውቀዋል። 

ከመከላከያ ሰራዊት የተገኘው መረጃ እንዳመላከተው እንግዶቹ በቆይታቸውም በተለያዩ ሁለትዮሽ ጉዳዩች እና በጋራ ስራዎች ላይ የተሞክሮ ልውውጥ ያደርጋሉ፡፡ 

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

ከዚህ ቀደም ነሃሴ 30፣ 2015 ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ የደቡብ አፍሪካው ኢታማዦር ሹም ጄነራል ሩድዛኒ ማፕህዋንያ ጋር በደቡብ አፍሪካ መወያየታቸው ይታወሳል። ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ከደቡብ አፍሪካ መከላከያ ሚኒስትር  ጋር  ባደረጉት ውይይት በሁለቱ ሀገራት እና ሕዝቦች መካከል ረጅም ዓመታትን ያስቆጠረው ታሪካዊ ግንኙነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጎለበተ ለመጣው ወታደራዊ ትብብር ጠንካራ መሰረት የጣለ መሆኑን አንስተዋል። 

በቀጣይ የትብብሮቹን አድማስ ለማስፋትና ወደላቀ ደረጃ ለማሸጋገር በቁርጠኝነት እንደሚሰሩም አረጋግጠዋል መባሉ ይታወሳል።አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button