ዜናፖለቲካ

ዜና: በኢትዮጵያ በቀጣይ በየሶስት ወሩ ቢያንስ በ10 በመቶ የኤሌክትሪክ ታሪፍ እንደሚጨምር ተጠቆመ

አዲስ አበባ፣ ነሃሴ 9/2016 ዓ.ም፡- የኢትዮጵያ መንግሥት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍን በየሶስት ወሩ ቢያንስ በ10 በመቶ ለመጨመር መዘጋጀቱ ተጠቆመ፤ መንግሥት የአራት ዓመታት የኤሌክሪክ ታሪፍ ማሻሻያ ማጽደቁም ተገልጿል።

የታሪፍ ጭማሪው የኢትዮጵያ መንግሥት ከዓለም ባንክ ጋር በተፈራረመው እርዳታ እና ብድር ሊከናወኑ ከታቀዱ ሥራዎች መካከል አንዱ መሆኑም ተገልጿል።

ዓለም ባንክ ይፋ ያደረገው ሰነድ ጠቅሶ ቪኦኤ ባስነበበው ዘገባው የኢትዮጵያ መንግሥት የአራት ዓመታት የኤሌክሪክ ታሪፍ ማሻሻያ ማጽደቁን አመላክቷል።

በማሻሻያው መሠረት በመጀመሪያው ዓመት ብቻ በየሶስት ወሩ ደንበኞች ለኤሌክትሪክ አገልግሎት የሚከፍሉት ታሪፍ ቢያንስ በ10 በመቶ ይጨምራ።

የዕቅዱ የመጨረሻ ግብ በሚቀጥሉት አራት ገደማ ዓመታት ማለትም እስከ ጎርጎሮሳዊው 2028 የሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ዘርፍ የሥራ ማስኬጃ እና የዕዳ ክፍያ ወጪውን ሙሉ በሙሉ እንዲመልስ ማድረግ መሆኑን ዘገባው ጠቁሟል።

በኢትዮጵያ ከጎርጎሮሳዊው 2006 እስከ 2018 ባሉት ዓመታት የኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ ምንም አይነት ለውጥ እንዳልተደረገበት ዓለም ባንክ ይፋ ያደረገው ሰነድ ጠቅሶ ዘገባው አስታውሷል።

በሰነዱ መሠረት ከ2018 እስከ 2021 ባሉት ዓመታት በአንጻሩ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ክፍያ በ180 በመቶ እንዲጨምር መደረጉን ያስታወቀው ዘገባው ይሁንና መንግሥት የሚሰበስበው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ ከተቋማቱ የሥራ ማስኬጃ እና የዕዳ ክፍያ መሸፈን የቻለው 18 በመቶ ብቻ መሆኑን አመላክቷል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የሰጠው 2.8 ቢሊዮን ዶላር ገደማ ብድር የተበላሸ ብድር እንደሆነ የዓለም ባንክ ሰነድ ያሳያል ያለው ዘገባው ታላቁ የኅዳሴ ግድብን ጨምሮ ግዙፍ የኃይል ማመንጫዎች በማስገንባት ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በተለይ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ቅርቃር ውስጥ ከከተቱ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች አንዱ መሆኑን አስታውቋል።

ከባንኮች አጠቃላይ ሐብት 58 በመቶ ገደማ ድርሻ ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደ የኢትዮጵያ ኤክትሪክ ኃይል ላሉ ተቋማት በሰጠው የተበላሸ ብድር ምክንያት ከፍተኛ ችግር ውስጥ ወድቋል ብሏል።

መንግሥት በበኩሉ የንግድ ባንክን ካፒታል ለማሳደግ እና የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ዕዳ ለመሰረዝ የ870 ቢሊዮን ብር ቦንድ እንዳወጣ ዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት ይፋ ያደረገው ሰነድ ያሳያል ያለው ዘገባው በቦንድ መልክ የተሰጠው 870 ቢሊዮን ብር የዕዳ እና ሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የነበረባቸውን የንግድ ባንክ ዕዳ ሙሉ በሙሉ የሚሰርዝ መሆኑን አስታውቋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button