ዜናፖለቲካ

ዜና: “ኢትዮጵያ በትክክለኛ አቅጣጫ እየተጓዘች ነው”፣ እርቅ ለማድረግ እየሄደችበት ያለው መንገድ ተስፋ ሰጪ ነው – ማይክ ሀመር

አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 10/2016 ዓ.ም፡- ኢትዮጵያ ሰላም እና እርቅ ለማምጣት እየሄደችበት ያለው አካሄድ ተስፋ ሰጪ በመሆኑ ሊበረታታ ይገባል ሲሉ በአፍሪካ ቀንድ የአሜሪካን መንግስት ልዩ ልዑክ ማይክ ሀመር አስታወቁ።

“ኢትዮጵያ በትክክለኛ አቅጣጫ እየተጓዘች ነው” ሲሉ የገለጹት ልዩ ልዑኩ በትግራይ ከቀያቸው የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀያቸው መመለስ መጀመራቸውን በአብነት አንስተዋል፤ በትግራይ የነበረው የሰብአዊ መብት ጥሰት እጅግ ቀንሷል ሲሉም ገልጸዋል።

በአማራ እና ኦሮምያ ክልል የቀጠለው ግጭት እንደሚያሳስባቸው ገልጸው በድርድር ሰላም ለማምጣት ለሚደረገው ጥረት አሜሪካ ዕገዛ ለማድረግ ዝግጁ ናት ማለታቸውንም ቪኦኤ ያስነበበው ቃለምልልስ ያሳያል።

በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ጸጥ ያሉት የጦር መሳሪያዎች አሁንም ከ20 ወራት በኋላ ጸጥ እንዳሉ ነው ሲሉ የገለጹት ማይክ ሀመር ይህም ትልቅ ስኬት ነው ምክንያቱ ከዚያ በፊት ይካሄድ የነበረው የአለማችን ዋነኛው ደም አፋሳሽ ጦርነት ነበር እና ሲሉ ጠቁመዋል። አሁንም ብዙ የሚቀሩ ጉዳዮች እንዳሉ እናውቃለን፣ ለምሳሌ ተፈናቃዮችን ሙሉ በሙሉ መመለስ እና የቀድሞ ታጋዮችን ትጥቅ ማስፈታታ እና ወደ ህብረተሰቡ መቀላቀል የሚሉት ቀሪ ስራዎች ናቸው ብለዋል።

በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት የተሳተፉ አካላት ቃላቸውን እንደጠበቁ ነውን ተብለው በቪኦኤ የተጠየቁት ሀመር የኢትዮጵያ መንግስት እና የህወሓት ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ስምምነቱን ለማስፈጸም ቁርጠኞች ናቸው፤ ዋናው አስፈላጊ ነገር ይሄ ነው፣ ለተግባራዊነቱ ቀጣይነት ወሳኝ ነው ሲሉ ጠቁመዋል።

አሁን ላይ ሁሉም የስምምነቱ ነጥቦች አልተተገበሩም ሲሉ የገለጹት ሀመር ለዚህም ነው አሜሪካ አሁንም በጉዳዩ ዙሪያ እየሰራች ያለችው፣ ሁለቱም አካላት የሚጠበቅባቸውን እንዲወጡ ጫና እያደረግን እንገኛለን ብለዋል። አስ

Download the First Edition of Our Quarterly Journal
ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button