ማህበራዊ ጉዳይዜናፖለቲካ

ዜና: የትግራይ ክልል ግብርና ቢሮ የደቡብ እና ምዕራብ ትግራይ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶችን ታሳቢ ያደረገ የ2016/17 የምርት ዘመን ዝግጅት እያደረኩ ነው አለ

አዲስ አበባ፣ ሰኔ 11/2016 ዓ.ም፡-በትግራይ ክልል በ2016/17 የምርት ዘመን አንድ ነጥብ ሶስት ሚሊየን ሄክታር በዘር በመሸፈን 24 ሚሊየን ኩንታል ለማምረት እቅድ ይዞ ወደ ስራ መግባቱን የክልሉ የእርሻ እና ተፈጥሮ ሀብት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር እያሱ አብርሃ አስታወቁ።

እቅዱ እጅግ የተለጠጠ መሆኑን ሃላፊው ጠቁመው በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት መሰረት የደቡብ እና ምዕራብ የክልሉ ሰፋፊ የእርሻ መሬቶች ሙሉ በሙሉ ይመለሳሉ፣ አምራች የሆነው ከአከባቢው የተፈናቀለቅ ነዋሪም ወደ ቀየው ይመለሳል በሚል ታሳቢ ተደርጎ የታቀደ መሆኑን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም እቅዱ የተዘጋጀው ባለፉት የበጋ ግዜያት በክልሉ በተከናወነው የአፈር ልማት ስራዎች ላይ አርሶ አደሩ ያሳየው ዝግጁነት ነው ሲሉ ገልጸዋል።

ክልሉ ያሉትን ሀብቶች በሙሉ አሟጦ በመጠቀም ልናሳካው እንችላለን ሲሉም አመላክተዋል።

ዋናው ጉዳይ ለግብርና ስራው አስፈላጊ የሆኑ ግብአቶች ወደ አርሶ አደሩ መድረሱ ነው ሲሉ የገለጹት ዶ/ር እያሱ በተያዘው አመት በቂ ማዳበሪያ ወደ ክልሉ በማስገባት ቀደምብሎ ዝግጅት የተደረገ በመሆኑ ለአርሶ አደሩ እየተዳረሰ ይገኛል ብለዋል።

ዘመናዊ ማዳበሪያ በህብረት ስራ ማህበራት እና በዩኒየኖች አመካኝነት እንደሚከፋፈል ገልጸው ከዚህ ውጭ ለማከፋፈል መሞከር በህግ ተጠያቂ ያደርጋል ሲሉ አሳስበዋል።

150ሺ ኩንታል ምርጥ ዘር ለማቅረብ 100 ሚሊየን ብር እንደተመደበ ጠቁመው ለዚህም የግብረሰናይ ድርጅቶች፣ ክልሎች እና ባለሀብቶች እገዛቸውን እንዲያጠናክሩ ጥሪ ማቅረባቸውን የህወሓት ልሳን ከሆነው ከወይን ጋዜጣ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

Download the First Edition of Our Quarterly Journal

 በትግራይ በተካሄደው ጦርነት ሳቢያ የክልሉ አርሶ አረድ ለማረሻ የሚሆኑ መሳሪያዎች እና በሬዎቹን በስፋት አጥቷል ሲሉ ገልጸው ይህንንም ችግር ለመቅረፍ የሜካናይዜሽን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ጥረት እየተደረገ ይገኛል ብለዋል።

እስካሁን 22 ትራክተር ለሰሜን ምዕራብ ዞን፣ 15 ትራክተር ለማዕከላዊ ዞን፣ 14 ትራክተር ለደቡብ ዞን፣ 10 ትራክተር ለደቡብ ምስራቅ፣ 5 ትራክተሮች ደግሞ ለምስራቅ ዞን በማቅረብ የማረስ ስራ እንዲሰሩ ይገኛሉ ሲሉ አስታውቀዋል። አስ

ተጨማሪ አሳይ

ተዛማጅ ጽሑፎች

Back to top button